አስቴር 10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምየንጉሥ አርጤክስስና የመርዶክዮስ ታላቅነት 1 ንጉሥ አርጤክስስ በንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛቱ ክልል ከጠረፍ እስከ ጠረፍ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ ግብር ጣለ። 2 እርሱ ያደረጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ መርዶክዮስንም ከፍ ከፍ በማድረግ እንዴት ወደ ታላቅ ማዕርግና ልዕልና እንዳደረሰው የሚገልጠው ታሪክ በፋርስና በሜዶን ነገሥታት የታሪክ መዝገብ ላይ በጽሑፍ እንዲሰፍር ተደርጓል። 3 አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ደረጃ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበር፤ እርሱም በወገኖቹ በአይሁድ ዘንድ በጣም የተከበረና የተወደደ ሰው ነበር፤ መርዶክዮስ ለወገኖቹና ለዘሮቻቸው በሰላም የመኖር ዋስትና ለማስገኘት በብርቱ የደከመ ሰው ነበር። |