Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የብንያም ትውልድ

1 ብንያም አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም በየዕድሜአቸው ተራ፥ ቤላዕ፥ አሽቤል፥ አሕራሕ፥

2 ኖሐና ራፋ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

3 የቤላዕ ዘሮች አዳር፥ ጌራ፥ አቢሁ፥

4 አቢሹዓ፥ ናዕማን፥ አሖሐ፥

5 ጌራ፥ ሸፉፋንና ሑራም ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

6-7 የኤሁድ ዘሮች ናዕማን፥ አሒያና ጌራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጌባዕ ይኖሩ ለነበሩት በኋላ ግን ከዚያ ተባረው ወደ ማናሐት ሄደው በዚያ ለኖሩ ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ ወደዚያም የመራቸው የዑዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበር።

8-9 ሻሐራም፥ ሑሺምና ባዕራ ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ሚስቶቹን ፈታ፤ ዘግየት ብሎም በሞአብ አገር ሲኖር ሖዴሽ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት አግብቶ ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዮባብ፥ ጺብያ፥ ሜሻ፥ ማልካም፥

10 የዑጽ፥ ሳክያና ሚርማ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ የእርሱ ወንዶች ልጆች በሙሉ የቤተሰብ አለቆች ሆኑ።

11 በተጨማሪም ሑሺም ከተባለችው ሚስቱ አሂቱብና ኤልፓዓል ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።

12 ኤልፓዓልም ዔቤር፥ ሚሸዓምና ሼሜድ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሼሜድም ኦኖና ሎድ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች የሠራ ነው።


በጋትና በአያሎን ይኖሩ የነበሩ ብንያማውያን

13 በሪዓና ሴማዕ በአያሎን ከተማ ለሰፈሩት ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም በጋት ከተማ የሚኖረውን ሕዝብ አባረሩ፤

14 የበሪዓ ዘሮች አሕዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬሞት፥

15 ዘባድያ፥ ዐራድ፥ ዔዴር፥

16 ሚካኤል፥ ዩሽፓና ዮሐ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ብንያማውያን

17 የኤልፓዓል ልጆች ዘባድያ፥ መሹላም፥ ሒዝቂ፥ ሔቤር፥

18 ዩሽመራይ፥ ዩዝሊአና ዮባብ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

19 የሺምዒ ልጆች ያቂም፥ ዚክሪ፥ ዛብዲ፥

20 ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥

21 ዐዳያ፥ በራያና ሺምራት ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

22 የሻሻቅ ልጆች ኢሽጳን፥ ዔቤር፥ ኤሊኤል፥

23 ዓብዶን፥ ዚክሪ፥ ሐናን፥

24 ሐናንያ፥ ዔላም፥ ዓንቶቲያ፥

25 ዩፍደያና ፋኑኤል ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

26 የይሮሐም ልጆች ሻምሸራይ፥ ሸሐርያ፥ ዐታልያ፥

27 ያዕሬሽያ፥ ኤሊያና ዚክሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

28 እነዚህ ሁሉ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ለነበሩት ቀደም ያሉ የቤተሰብ አለቆችና የእነርሱም ዋና ዋና ዘሮች ናቸው።


በገባዖንና በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ብንያማውያን

29 ይዒኤል የገባዖንን ከተማ ቈርቊሮ በዚያው ኖረ፤ ሚስቱ ማዕካ ተብላ የምትጠራ ስትሆን፥

30 የበኲር ልጁም ዓብዶን ይባል ነበር፤ ሌሎቹ የእርሱ ወንዶች ልጆች ጹር፥ ቂሽ፥ ባዓል፥ ኔር፥ ናዳብ፥

31 ገዶር፥ አሕዮ፥ ዜኬርና፥

32 የሺምዓ አባት ሚቅሎት ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ የእነርሱም ዘሮች በሌሎቹ የጐሣቸው ቤተሰቦች አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር።


የንጉሥ ሳኦል ቤተሰብ

33 ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ንጉሥ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታን፥ ማልኪሹዓ፥ አቢናዳብና ኤሽባዓል ተብለው የሚጠሩትን አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤

34 ዮናታንም መሪባዓልን ወለደ፤ መሪባዓልም ሚካን ወለደ።

35 ሚካም ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓና አሐዝ ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆች ወለደ።

36 አሐዝ የሆዓዳን ወለደ፤ የሆዓዳም ዓሌሜት፥ ዓዝማዌትና ዚምሪ ተብለው የሚጠሩትን ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዚምሪም ሞጻን ወለደ፤

37 ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ራፋን ወለደ፤ ራፋ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳም አጼልን ወለደ።

38 አጼልም ዓዝሪቃም፥ ቦከሩ፥ እስማኤል፥ ሸዓርያ፥ አብድዩና ሐናን ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤

39 የአጼል ወንድም ዔሼቅም በኲሩ ኡላም፥ ሁለተኛው ያዑሽና ሦስተኛ ኤሊፌሌጥ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ።

40 የኡላም ወንዶች ልጆች ዝነኛ ወታደሮችና ቀስት ወርዋሪዎች ነበሩ፤ የእነርሱም ዘሮች በአጠቃላይ አንድ መቶ ኀምሳ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ፤ እንግዲህ ከዚህ በላይ ስሞቻቸው የተጠቀሱት ሁሉ የብንያም ነገድ ነበሩ።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告