1 ዜና መዋዕል 6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምየሊቀ ካህናት ቤተሰብ የትውልድ ሐረግ 1 የሌዊ ልጆች እነርሱም ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤ 2 ቀዓትም ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ። 3 ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት። 4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሹዓን ወለደ፤ አቢሹዓ ቡቂን ወለደ፤ 5 ቡቂ ዑዚን ወለደ፤ 6 ዑዚ ዘራሕያን ወለደ፤ ዘራሕያ መራዮትን ወለደ፤ 7 መራዮት አማርያን ወለደ፤ አማርያ አሒጦብን ወለደ፥ 8 አሒጦብ ጻዶቅን ወለደ፤ ጻዶቅ አሒማዓጽን ወለደ፤ 9 አሒማዓጽ አዛርያስን ወለደ፤ ዓዛርያስም ዮሐናን ወለደ፤ 10 ዮሐና ዓዛርያስን ወለደ፤ አዛርያስ ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለግል የነበረ ነው። 11 ዐዛርያስ አማርያን ወለደ፤ አማርያ አሒጡብን ወለደ፤ 12 አሒጡብ ጻዶቅን ወለደ፤ ጻዶቅ ሻሉምን ወለድ፤ 13 ሻሉም ሒልቂያን ወለደ፤ ሒልቂያ ዐዛርያስን ወለደ፤ 14 ዐዛርያስ ሤራያን ወለደ፤ ሤራያም ኢዮጼዴቅን ወለደ። 15 እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር ተማርከው በስደት እንዲኖሩ ባደረገ ጊዜ ኢዮጼዴቅም ከእነርሱ ጋር ተማርኮ ሄደ። የሌዊ ትውልድ 16 ሌዊ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ 17 ጌርሾንም ሊብኒንና ሺምዒን ወለደ፤ 18 ቀዓትም ዓምራምን፥ ይጽሐርን፥ ኬብሮንንና ዑዚኤልን ወለደ፤ 19 መራሪ ደግሞ ማሕሊንና ሙሺን ወለደ። የሌዊ የነገድ ወገኖች በየትውልዳቸው የሚከተሉት ናቸው፦ 20 ጌርሾን ሊብኒን ወለደ፤ ሊብኒ ያሐትን ወለደ፤ ያሐት ዚማን ወለደ፤ 21 ዚማ ዮአሕን ወለደ፤ ዮአሕ ዒዶን ወለደ፤ ዒዶ ዜራሕን ወለደ፤ ዜራሕም የአትራይን ወለደ። 22 የቀዓት ዘሮች፦ ቀዓት ዐሚናዳብን ወለደ፤ ዐሚናዳብ ቆሬን ወለደ፤ ቆሬ አሲርን ወለደ፤ 23 አሲር ኤልቃናን ወለደ፤ ኤልቃና ኤቢያሳፍን ወለደ፤ ኤቢያሳፍ አሲርን ወለደ፤ 24 አሲር ታሐትን ወለደ፤ ታሐት ኡሪኤልን ወለደ፤ ኡሪኤል ዑዚያን ወለደ፤ ዑዚያም ሻኡልን ወለደ። 25 የኤልቃና ዘሮች ኤልቃናም ዐማሣይንና አሒሞትን ወለደ፤ 26 አሒሞትም ኤልቃናን ወለደ፤ ኤልቃናም ጾፋይን ወለደ፤ ጾፋይ ናሐትን ወለደ፤ 27 ናሐት ኤሊያብን ወለደ፤ ኤልያብ ይሮሐምን ወለደ፤ ይሮሐምም ሕልቃናን ወለደ። 28 የሳሙኤል ልጆች፦ ሳሙኤል ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም በኲሩ ኢዩኤል ሁለተኛው አቢያ ተብለው ይጠሩ ነበር። 29 የመራሪ ዘሮች፦ መራሪ ማሕሊን ወለደ፤ ማሕሊ ሊብኒን ወለደ፤ ሊብኒ ሺምዒን ወለደ ሺምዒ ዑዛን ወለደ፤ 30 ዑዛ ሺምዓን ወለደ፤ ሺምዓ ሐጊያን ወለደ፤ ሐጊያም ዐሳያን ወለደ። የቤተ መቅደስ መዘምራን 31 የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት ለሚያገለግሉት መዘምራን ኀላፊ የሚሆኑ ሰዎችን ሾመ፤ 32 ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ከመሥራቱ በፊት እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን የመዘመር ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፤ የሥራቸውንም ቅደም ተከተል በተዘጋጀላቸው ተራ መሠረት ይፈጽሙ ነበር። 33 በዚህ ቦታ ተመድበው የሚያገለግሉት ሰዎች የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦ የቀዓት ጐሣ፦ የመጀመሪያው የመዘምራን ቡድን መሪ ኢዩኤል ልጅ ዘማሪው ሄማን ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ያዕቆብ ይደርሳል፦ ሄማን፥ ዮኤል፥ ሳሙኤል፥ 34 ሕልቃና፥ ይሮሐም፥ ኤሊኤል፥ ቶሐ፥ 35 ጹፍ፥ ኤልቃና፥ ማሐት፥ ዐማሣይ፥ 36 ኤልቃና፥ ኢዩኤል፥ ዐዛርያ፥ ሶፎንያስ፥ 37 ታሐት፥ አሲር፥ ኤቢያሳፍ፥ ቆሬ፥ 38 ይጽሐር፥ ቀዓት፥ ሌዊ፥ ያዕቆብ። 39 በቀኙ በኩል የቆመው የሁለተኛው የመዘምራን ቡድን መሪ አሳፍ ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ሌዊ ይደርሳል፦ አሳፍ፥ በራክያ፥ ሺምዓ፥ 40 ሚካኤል፥ ባዕሴያ፥ ማልኪያ፥ 41 ኤትኒ፥ ዜራሕ፥ ዐዳያ፥ 42 ኤታን፥ ዚማ፥ ሺምዒ፥ 43 ያሐት፥ ጌርሾን፥ ሌዊ። 44 በግራው በኩል የቆመው የሦስተኛው የመዘምራን ቡድን መሪ የመራሪ ልጅ ኤታን ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ሌዊ ይደርሳል፦ ኤታን፥ ቂሺ፥ ዐብዲ፥ ማሉክ፥ 45 ሐሻብያ፥ አሜስያስ፥ ሒልቂያ፥ 46 አሞጺ፥ ባኒ፥ ሼሜር፥ 47 ማሕሊ፥ ሙሺ፥ መራሪ፥ ሌዊ። 48 ሌዋውያን የሆኑ የእነርሱ ወገኖችም በእግዚአብሔር ቤት ሌላውን ተግባር ሁሉ ያከናውኑ ነበር። የአሮን ትውልድ 49 አሮንና ዘሮቹ የዕጣን መባና በመሠዊያው ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ ያቀርቡ ነበር፤ እንዲሁም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የአምልኮ ሥርዓትና እግዚአብሔር የእስራኤልን ኃጢአት ለሚያስተሰርይበት መሥዋዕት ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ፤ እነርሱም ይህን ሁሉ የሚፈጽሙት እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለሙሴ በሰጠው መመሪያ መሠረት ነው። 50 የአሮን ዘሮች የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው፦ አልዓዛር፥ ፊንሐስ፥ አቢሹዓ፥ 51 ቡቂ፥ ዑዚ፥ ዘራሕያ፥ 52 መራዮት፥ አማርያ፥ አሒጦብ፥ 53 ሳዶቅ፥ አሒማዓጽ። ለሌዋውያን የተሰጡ መኖሪያ ስፍራዎች 54 ለአሮን ልጆች የተመደቡት የሰፈራ ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤ የመጀመሪያው ዕጣ ለቃሃት ወገን ስለ ወጣ 55 ለእርሱም የተሰጠው ድርሻ በይሁዳ ግዛት የሚገኘው ኬብሮንና በእርሱም ዙሪያ ያለውን የግጦሽ ቦታ ሁሉ ያጠቃልላል። 56 የኬብሮን የእርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ የተመደቡ ነበሩ። 57-59 ለአሮን ልጆች የተመደቡ ከተሞች፥ የመማጠኛ ከተማ የሆነችው ኬብሮን፥ ያቲር፥ ሊብና፥ ኤሽተሞዓ፥ ሒሌን፥ ደቢር፥ ዐሻንና ቤትሼሜሽ ሲሆኑ የግጦሽ ቦታዎቻቸውንም ይጨምራል። 60 በብንያም ግዛትም ጌባዕ፥ ዓሌሜትና ዐናቶት ተብለው የሚጠሩት ከተሞች ከነግጦሽ ቦታዎቻቸው ለአሮን ልጆች የተሰጡ ነበሩ፤ እንግዲህ ለአሮን ዘሮች ቤተሰብ ሁሉ መኖሪያ የሚሆኑ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ነበሩ። 61 በምዕራብ በኩል ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ግዛት ዐሥር ከተሞች ለቀሩት ለቀዓት ወገን ተሰጡ። 62 ለጌርሾን ጐሣም ከይሳኮር፥ ከአሴር፥ ከንፍታሌምና በባሳን ካለው ከምሥራቅ ምናሴ ግዛቶች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ለየቤተሰቡ ተመድበው ነበር። 63 እንዲሁም ለመራሪ ጐሣ በየወገናቸው ከሮቤል፥ ከጋድና ከዛብሎን ግዛቶች በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመድበው ነበር። 64 በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ ሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞች መደቡላቸው፤ ይህም በየከተማው ዙሪያ ያለውን የግጦሽ ቦታ ያጠቃልላል። 65 ከላይ የተጠቀሱት በይሁዳ፥ በስምዖንና በብንያም ግዛቶች ውስጥ የሚገኙት ከተሞች እንደ ሌሎቹ ሁሉ በዕጣ የተመደቡ ነበሩ። 66 ከቀዓት ጐሣ አንዳንድ ቤተሰቦች በኤፍሬም ግዛት ውስጥ ከተሞችና የግጦሽ ቦታዎች ተመድበውላቸው ነበር። 67 እነርሱም በኤፍሬም ኰረብቶች የምትገኘው የመማጠኛ ከተማ የሆነችው ሴኬም፥ ጌዜር፥ 68 ዮቅመዓም፥ ቤትሖሮን፥ 69 አያሎንና ጋትሪሞን ከግጦሽ መሬታቸው ጋር ናቸው። 70 በምዕራብ በኩል ባለው በምናሴ ግዛት ደግሞ የዓኔርና የቢልዓም ከተሞች በዙሪያቸው ካሉት የግጦሽ ቦታዎች ጋር ለቀሩት ለቀዓት ጐሣ ቤተሰቦች ተመድበውላቸው ነበር። 71 ለጌርሾን ጐሣ ቤተሰቦች የሚከተሉት ከተሞች በዙሪያቸው ከሚገኙት የግጦሽ ቦታዎች ጋር ተመድበውላቸው ነበር፦ በምሥራቅ በኩል ካለው ከምናሴ ግዛት በባሳን ያለው ጎላንና ዐስታሮት። 72 በይሳኮር ግዛት፥ ቃዴስ፥ ዳበራት፥ 73 ራሞትና ዓኔም። 74 በአሴር ግዛት ማሻል፥ ዓብዶን፥ 75 ሑቆቅና ረሖብ፤ 76 በንፍታሌም ግዛት በገሊላ ምድር የምትገኘው ቄዴሽ፥ ሐሞንና ቂርያታይም፤ 77 ለቀሪዎቹ የመራሪ ጐሣ ቤተሰቦች የሚከተሉት ከተሞች በዙሪያቸው ከሚገኙት የግጦሽ ቦታዎች ጋር ተመድበውላቸው ነበር፦ በዛብሎን ግዛት ሪሞኖና ታቦር፤ 78 ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ ከኢያሪኮ ማዶ ባለው በሮቤል ግዛት በከፍተኛ ሜዳ ላይ የምትገኘው ቤጼር፥ ያህጻ፥ 79 ቀዴሞትና ሜፋዓት፤ 80 በጋድ ግዛት በገለዓድ የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥ 81 ሐሴቦንና ያዕዜር። |