Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የንጉሥ ዳዊት ትውልድ

1-3 ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤

4 እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት በኬብሮን ሲሆን ዳዊት መኖሪያውን በዚያ አድርጎ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ወቅት ነው። ዳዊት መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ ሦስት ዓመት ገዛ፤

5 በዚያም ብዙ ወንዶች ልጆችን ወለደ። የዓሚኤል ልጅ ቤርሳቤህ ሺምዓ፥ ሾባብ፥ ናታንና ሰሎሞን ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት።

6 ሌሎች ዘጠኝ ወንዶች ልጆችም ነበሩት፤ እነርሱም ይብሐር፥ ኤሊሹዓ፥ ኤሊፋሌጥ፥

7 ኖጋህ፥ ኔፌግ፥ ያፊዓ፥

8 ኤሊሻማዕ፥ ኤሊያዳዕና ኤሊፌሌጥ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤

9 ከእነዚህም ሌላ ዳዊት ከቊባቶቹ የወለዳቸው ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ትዕማር ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅም ነበረችው።


የንጉሥ ሰሎሞን ትውልድ

10 የንጉሥ ሰሎሞን የትውልድ ሐረግ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፥ ሰሎሞን፥ ሮብዓም፥ አቢያ፥ አሳ፥ ኢዮሣፍጥ፥

11 ኢዮራም፥ አካዝያስ፥ ኢዮአስ፥

12 አሜስያስ፥ ዐዛርያስ፥ ኢዮአታም፥

13 አካዝ፥ ሕዝቅያስ፥ ምናሴ፥

14 አሞንና ኢዮስያስ፤

15 የኢዮስያስም ልጆች በኲሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛው ኢዮአቄም፥ ሦስተኛው ሴዴቅያስና አራተኛው ሻሉም ናቸው፤

16 ኢዮአቄም ደግሞ ኢኮንያንና ጼዴቅያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።


የንጉሥ ኢኮንያን የትውልድ ሐረግ

17-18 የባቢሎን ምርኮኛ የነበረው የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ ማልኪራም፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማዕና ነዳብያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

19 ፈዳያም ዘሩባቤልና ሺምዒ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዘሩባቤልም መሹላምና ሐናንያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ሰሎሚት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ነበሩት።

20 እንዲሁም ሌሎች አምስት ወንዶች ልጆች ሲኖሩት፥ እነርሱም ሐሹባ፥ ኦሔል፥ ቤሬክያ፥ ሐሳድያና ዩሻብሔሴድ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

21 ሐናንያም ፈላጥያና ይሻዕያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ይሻዕያም ረፋያን ወለደ፤ ረፋያም አርናንን ወለደ፤ አርናን አብድዩን ወለደ፤ አብድዩም ሸካንያን ወለደ፤

22 ሸካንያም ሸማዕያን ወለደ፤ ሸማዕያም ሐጡሽ፥ ዩጋል፥ ባሪያሕ፥ ነዓርያና ሻፋጥ ተብለው የሚጠሩትን አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የሸካያ ትውልድ በድምሩ ስድስት ነበር፤

23 ነዓርያም ኤልዮዔናይ፥ ሕዝቅያስና ዓዝሪቃም ተብለው የሚጠሩትን ሦስት ልጆችን ወለደ፤

24 ኤልዮዔናይም ሆዳውያ፥ ኤልያሺብ፥ ፐላያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያና ዐናኒ ተብለው የሚጠሩትን ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告