Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የቤተ መቅደስ መዘምራን

1 ንጉሥ ዳዊትና የሌዋውያን አለቆች የአሳፍን፥ የሔማንና የይዱቱን ልጆች መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን መዝሙር በመሰንቆ፥ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ እንዲዘምሩ ለዩአቸው። ለዚህ አገልግሎት የተመደቡት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦

2 ዛኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያና አሳርኤላ ተብለው የሚጠሩት አራቱ የአሳፍ ልጆች ሲሆኑ፥ ንጉሡ ትእዛዝ ባስተላለፈ ቊጥር የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበለውን መዝሙር የሚያሰማው አሳፍ የእነርሱ መሪ ነበር።

3 ገዳልያ፥ ጸሪ፥ ያሻያ፥ ሺምዒ፥ ሐሻብያና ማቲትያ ተብለው የሚጠሩት ስድስቱ የይዱቱን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም በበገና ድምፅ እየታጀቡ በአባታቸው መሪነት የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበላቸውን መዝሙር እያሰሙ እግዚአብሔርን በዝማሬ ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።

4 ቀጥሎም ዐሥራ አራቱ የሄማን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም ቡቂያ፥ ማታንያ፥ ዑዚኤል፥ ሸቡኤል፥ ያሪሞት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤሊአታ፥ ጊዳልቲ፥ ሮማምቲዔዜር፥ ዮሽበቃሻ፥ ማሎቲ፥ ሆቲርና ማሕዚአት ናቸው፤

5 እግዚአብሔር የንጉሡ ነቢይ ለሆነው ለሄማን እነዚህን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችና ሦስት ሴቶች ልጆችን ጭምር ሰጠው፤ ይህንንም ያደረገው የሄማንን ኀይል ከፍ ለማድረግ ቀደም ሲል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።

6 ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በማጀብ በአባታቸው መሪነት ጸናጽል ያንሿሹና መሰንቆና በገና ይደረድሩ ነበር፤ አሳፍ፥ ይዱታንና ሄማን በንጉሡ ሥልጣን ሥር ነበሩ።

7 ከእነርሱም ጋር ለእግዚአብሔር አገልግሎት በዜማ መሣሪያ ያሠለጠኑ ዘመዶቻቸው ነበሩ፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ነበሩ።

8 የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር።

9-31 የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሁለተኛው ለገዳልያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ሦስተኛ ለዛኩር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፥ አምስተኛ ለነታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስድስተኛ ለቡቅያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሰባተኛ ለአሳርኤላ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስምንተኛው ለያሻዕያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዘጠነኛው ለማታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥረኛው ለሺምዒ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ አራተኛ ለማቲትያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አምስተኛው ለያሪሞት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሽ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ዘጠነኛ ለማሎቲ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያኛ ለኤሊአታ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አንደኛ ለሆቲር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሁለተኛ ለጊደልቲ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሦስተኛ ለማሕዚኦት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አራተኛ ለሮሚምቲዔዜር ወጣ፤ እርሱም ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告