1 ዜና መዋዕል 1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምከአዳም እስከ አብርሃም ያለው የትውልድ ሐረግ ( ዘፍ. 5፥1-32 ፤ 10፥1-32 ፤ 11፥10-26 ) 1 አዳም ሤትን ወለደ፤ ሤት ሄኖስን ወለደ፤ ሄኖስ ቃይናንን ወለደ፤ 2 ቃይናን መሀላልኤልን ወለደ፤ መሀላልኤል ያሬድን ወለደ፤ እነርሱም በየስማቸው ለሚጠሩ ሕዝቦች የቀድሞ አባቶች ናቸው። 3 ያሬድ ሔኖክን ወለደ፤ ሔኖክ ማቱሳላን ወለደ፤ ማቱሳላ ላሜሕን ወለደ፤ 4 ላሜሕ ኖኅን ወለደ፤ ኖኅ ሴምን፥ ካምንና ያፌትን ወለደ። 5 ያፌትም ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና ቲራስ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 6 የጎሜር ልጆች አሽከናዝ፥ ሪፋትና ቶጋርማ ናቸው። 7 የያዋን ልጆች፥ ኤሊሻ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም እና ሮዳሂም ናቸው። 8 የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው። 9 የኩሽ ልጆች ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሰብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው፤ የራዕማ ወንዶች ልጆች ሳባና ድዳን ናቸው። 10 ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ ናምሩድም በዓለም የመጀመሪያው ታዋቂ ጦረኛ ሆነ። 11 የምጽራይም ልጆች ሉዲም፥ አናሚም፥ ሌሃቢም ናፍቱሔም፥ 12 የፈትሩሲም፥ የከስሉሂምና የፍልስጥኤማውያን አባት የከፍቶሪም ሕዝቦች ናቸው። 13-16 የከነዓን የበኲር ልጅ ጺዶን ሲሆን እንዲሁም ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያን፥ ዓርቃውያን፥ ሲናውያን፥ አርዋዳውያን፥ ጸማራውያንና ሐማታውያን የከነዓን ልጆች ናቸው። 17 የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴርና ሜሼክ ሲሆኑ፥ እነርሱም በስሞቻቸው ለሚጠሩ ሕዝቦች የነገድ አባቶች ናቸው። 18 አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ፤ 19 ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ በእርሱ ዘመን የዓለም ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ የመጀመሪያው ልጅ ፌሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ሁለተኛው ደግሞ ዮቅጣን ተብሎ ተጠራ። 20 ዮቅጣን አልሞዳድን፥ ሼሌፍን፥ ሐጻርማዌትን፥ ዬራሕን፥ 21 ሀዶራምን፥ ኡዛልን፥ ዲቅላን፥ 22 ዔባልን፥ አቢማኤልን፥ ሳባን፥ 23 ኦፊርን፥ ሐዊላና ዮባብን ወለደ። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ። 24 ከሴም እስከ አብራም ያለው የትውልድ ሐረግ ሴምን፥ አርፋክስድን፥ ሼላሕን፥ 25 ዔቦርን፥ ፋሌቅን፥ ረዑን፥ 26 ሰሩግን፥ ናኮርን፥ ታራንና 27 በኋላ አብርሃም የተባለውን አብራምን ያጠቃልላል። የእስማኤል ትውልድ ( ዘፍ. 25፥12-16 ) 28 አብርሃም ይስሐቅንና እስማኤልን ወለደ፤ 29-30 የእስማኤል ልጆች በእስማኤል በኵር ልጅ ስም የተጠራው ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድበኤል፥ ሚብሣም፥ ሚሽማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ሐዳድ፥ ቴማ፥ 31 ይጡር፥ ናፊሽና ቄድማ ተብለው የሚጠሩት ናቸው። 32 አብርሃም ቀጡራ ተብላ ከምትጠራው ቊባቱ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ መዳን፥ ምድያም፥ ዩሽባቅና ሹሐ ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዮቅሻንም ሳባና ደዳን ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ 33 ሚድያምም ዔፋ፥ ዔፌር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ተብለው የሚጠሩትን አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የዔሳው ትውልድ ( ዘፍ. 36፥1-19 ) 34 የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ፥ ዔሳውንና ያዕቆብን ወለደ፤ 35 ዔሳውም ኤሊፋዝን፥ ረዑኤልን፥ ይዑሽን፥ ያዕላምንና ቆሬን ወለደ፤ 36 ኤሊፋዝም ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፊ፥ ጋዕታም፥ ቀናዝ፥ ቲምናዕና፥ ዐማሌቅ ተብለው የሚጠሩትን ልጆች ወለደ። 37 ረዑኤልም ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና፥ ሚዛ ተብለው የሚጠሩትን ልጆች ወለደ። የመጀመሪያዎቹ የኤዶም ነዋሪዎች ( ዘፍ. 36፥20-30 ) 38-42 የሤዒር ልጆች ሎጣን፥ ሸባል ጸባኦን፥ ዐና፥ ዲሾን፥ ኤጸርና ዲሻን ናቸው። የሎጣን ልጆች ሖሪ፥ ሆማም ሲሆኑ፥ ቲምና የሎጣን እኅት ነበረች። የሾባል ልጆች አልዋን፥ ማናሐት፥ ዔባል ሸፊ እና ኦናም ናቸው። የጸባኦን ልጆች አያ እና አና ናቸው። የአና ልጅ ዲሾን ነው። የዲሾንም ልጆች ሔምዳን፥ ኤሽባን፥ ኢትራን እና ክራን ናቸው። የኤጽር ልጆች ቢልሃን፥ ዛእዋን፥ ዓቃን ናቸው። የዲሻን ልጆች ዑፅ እና አራን ናቸው። የኤዶም ነገሥታት ( ዘፍ. 36፥31-43 ) 43 በእስራኤል ምንም ንጉሥ ባልነገሠበት ዘመን የሚከተሉት ነገሥታት በኤዶም ምድር በየተራ ነግሠዋል፦ የከተማው ስም ዲንሃባ ይባል የነበረው የበዖር ልጅ ቤላዕ ነገሠ፤ 44 ቤላዕም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ ባሶራዊው የዛራ ልጅ ዮባብ ነገሠ። 45 ዩባብ በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ሰው ሑሻም ነገሠ፥ 46 ሑሻም በሞተ ጊዜ በሞአብ አገር ምድያምን ያሸነፈው የበዳድ ልጅ ሀዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም አዊ ነበረ። 47 ሀዳድ በሞተ ጊዜ የማሥሬቃ ተወላጅ የነበረው ሳምላ ነገሠ። 48 ሳምላም በሞተ ጊዜ በኤፍራጥስ ወንዝ ዳር ያለችው የረሐቦት ተወላጅ የነበረው ነገሠ። 49 ሻኡል በሞተ ጊዜ የዐክቦር ልጅ የነበረው በዓልሐናን ነገሠ። 50 በዓልሐናን በሞተ ጊዜ የፋዑ ተወላጅ የነበረው ሀዳድ ነገሠ፤ ሚስቱም መሄጣብኤል የምትባል የዛሀብ የልጅ ልጅ የማናሬድ ልጅ ነበረች። 51 ሃዳድም ሞተ የኤዶምም አለቆች ቲምናዕ፥ ዐልዋ፥ ዬቴት 52 ኦሆሊባማ፥ ኤላ፥ ፊኖን፥ 53 ቀናዝ፥ ቴማን፥ ሚብዳር፥ 54 መግዲኤልና ዒራም ተብለው ይጠሩ ነበር። |