Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

መዝሙር 23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የዳዊት መዝሙር።

1 የዳዊት መዝሙር። ጌታ እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።

2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፥ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል

3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።

4 በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

5 በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬንም እስከ አፉ ሞላህ።

6 ቸርነትና ምሕረት በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘለዓለም እኖራለሁ።

跟着我们:



广告