Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

መዝሙር 100 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የምስጋና መዝሙር።

1 የምስጋና መዝሙር። ምድር ሁሉ፥ ለጌታ እልል በሉ፥

2 በደስታም ለጌታ ተገዙ፥ በእልልታም ወደ ፊቱ ግቡ።

3 ጌታ እርሱ አምላክ እንደሆነ እወቁ፥ እርሱ ሠራን፥ እኛም የእርሱ ነን፥ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን።

4 ወደ ደጆቹ በውዳሴ፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፥ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥

5 ጌታ ቸር፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።

跟着我们:



广告