ዘፍጥረት 44 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ ዓይበታቸው የሚያነሣውን ያህል እህል ሙላላቸው የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤ 2 በታናሹም ዓይበት አፍ የብሩን ጽዋዬና የእህሉን ዋጋ ጨምራው። 3 እርሱም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። ነገህ በሆነ ጊዜም ሰዎቹ አህዮቻቸውን ይዘው ይሄዱ ዘንድ ተሰናበቱ። 4 ከከተማይቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፦ ተነሥተህ ሰዎቹና ተከተላቸው በደረስህባቸውም ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ በመልካሙ ፋንታ፥ 5 ስለ ምን ክፋን መለሳችህ? ጌታዬ የሚጠጣበት ምሥጢርንም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? ባደረጋችሁች ነገር በደላችሁ። 6 እርሱም ደርሰባቸው ይህንም ቃል ነገራቸው። 7 እነርሱም አሉት፦ ጌታዬ እንደዚህ ያለው ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ያለውን ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ይህን ነገር የሚያደርጉ አይደሉም። 8 እነሆ በዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር ይዘን ከከነዓን አገር ወደ አንተ ተመልሰናል ከጌታህ ቤት ወርቅ ወይስ በር እንዴት እንሰርቃለን? 9 ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ይሙት እኛም ደግሞ ለጌታችን ባሪያዎች እንሁን። 10 እርሱም አለ፦ አሁንም እንዲህ እንደ ነገራችሁ ይሁን ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ንጽሐን ትሆናላችሁ፤ 11 እየራሳቸውም ፈጥነው ዓይበታቸውን ወደ ምድር አወረዱ፥ እየራሳቸውም ዓይበታቸውን ፈቱ። 12 እርሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረበራቸው ጽዋውንም በብንያም ዓይበት ውስጥ አገኘው። 13 ልብሳቸውንም ቀደዱ ዓይበታቸውንም በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ። 14 ይሁዳም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ እርሱም ገና ከዚያው ነበረ፤ በፊቱም በምድር ላይ ወደቁ። 15 ዮሴፍም ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድር ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥጢርን እንድያውቅ አታውቁምን? አላቸው። 16 ይሁዳም አለ፦ ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ እነሆ እኝም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበቱም ደግሞ ለጌታዬ ባሪያዎቹ ነን። 17 እርሱም እላቸው፦ ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ። 18 ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና። 19 ጌታዬ ባሪያዎቹን፦ አባት አላችሁን ወይስ ወንድም? ብሎ ጠየቀ። 20 እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልነ፦ ሸማግሌ አባት አለን በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ ወንድሙም ሞተ ከእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ አባቱም ይወድደዋል። 21 አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ። 22 ጌታዬንም፦ ብላቴናው አባቱን መተው አይሆንለትም የተወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞታልና አልነው። 23 ባርያዎችህንም፦ ታናሽ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዮም አልኽን። 24 ወደ ባርያህ ወደ አባታችን በተመለስን ጊዜም የጌታዮን ቃል ነገርነው። 25 አባታችንም፦ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱ ልን አለ። 26 እኛም አልነው፦ እንሄድ ዘንድ አይሆንልንም ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ይወርድ እንደ ሆነ እኝም እንወርዳለን ታናሹ ወንድማችን ከእኝ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና ባሪያን አባቴም እንዲህ አለን፦ 27 ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደ ወለደችልኝ እናንተ ታውቃላችሁ፤ 28 አንዱም ከእኔ ወጣ፦ አውሬ በላው አላችሁኝ እስከ ዛሬም አላየሁትም፤ 29 ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው ሽበቴን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። 30 አሁንም እኔ ወደ አባቴ ወደ ባሪያህ ብሄድ ብላቴናውም ከእኛ ጋር ከሌለ ነፍሱ በብላቴናው ነፍስ ታስራለችና ብላቴናው ለእን ጋር እንደሌለ ባየ ጊዜ ይሞታል 31 ባሪያዎህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በኅዘን ወደ መቃብር ያወርዳሉ። 32 እኔ ባሪያህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዮ ተውሼአለሁና፦ እርሱንስ ወደ አንተ ባለመጣው በአባቴ ሀዘኔ በዘመናት ሁሉ ኃጢአተኛ እሆናለሁ። 33 ስለዚህም እኔ ባሪያህ በጌታዬ ዘንድ ባሪያ ሆኜ በብላቴናው ፋንታ ልቀመጥ ብላቴናውም ከወንድሞቹ ጋር ይውጣ። 34 አለዚያም ብላቴናው ከእኔ ጋር ከሌለ ወደ አባቴ እንዴት እወጣለሁ? አባቴን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ። |