ዘፍጥረት 13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። 2 አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ። 3 ከአዜብ ባደረገው በጉዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤ 4 ያም ስፍራ አስቀድሞ መሠውይ የሠራበት ነው በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። 5 ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው። 6 በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም የነበራቸው እጅግ ነበረና በአንድነት ሊቀመጡ አልቻሉም። 7 የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያም ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር። 8 አብራምም ሎጥን አለው እኛ ወንድማምች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። 9 ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። 10 ሎጥም ዓይኑን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ። 11 ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥርቅ ተጓዘ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተሰያዩ። 12 አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜድ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ስዶም ሰዎች ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ። 13 የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ። 14 ሎጥ ከተለየው በኍላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፤ 15 ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። 16 ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል። 17 ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና። 18 አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ። |