Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ዘፍጥረት 11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።

2 ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ በዚያም ተቀመጡ።

3 እርስ በርሳቸውም፤ ኑ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኩስው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፍት እንደ ጭቃ ሆነችላችው።

4 እንዲህም፤ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስምችንን እናስጠራው አሉ።

5 እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።

6 እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ እነርሱ አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

7 ኑ፥ እንውረድ፤ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚይ እንደባልቀው።

8 እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።

9 ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።

10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኍላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ።

11 ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኍላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

12 አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥

13 ቃይንምንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይንምንም ከወለደ በኍላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችም ወለደ፥ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶቸም ወለደ፤ ሞተም።

14 ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤

15 ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኍላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።

16 ዔበርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥

17 ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔበርም ፋሌቅን ከወለደ በኍላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

18 ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥

19 ራግውንም ወለደ፤ ራግውንም ከወለደ በኍላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

20 ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥

21 ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኍላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

22 ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥

23 ናኮርንም ወለደ፤ ናኮርንም ከወለደ በኍላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

24 ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥

25 ታራንም ወለደ፤ ታራንም ከወለደ በኍላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ወንዶችን ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

26 ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።

27 የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራም አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ።

28 ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ።

29 አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዩስካ አባት ነው።

30 ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።

31 ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፤ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።

32 የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።

跟着我们:



广告