Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘካርያስ 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በዚያ ቀን በረዶ፣ ውርጭና ብርሃን አይኖርም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ አይኖርም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዚያን ዘመን ውርጭና ዐመዳይ ጨለማም ከቶ አይኖርም፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘካርያስ 14:6
24 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብ​ሩም ከሰ​ማ​ያት በላይ ነው።


የሰ​ማ​ይም ከዋ​ክ​ብ​ትና ኦሪ​ዎን፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትም ሁሉ ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም፤ ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ ትጨ​ል​ማ​ለች፤ ጨረ​ቃም በብ​ር​ሃኑ አያ​በ​ራም።


ጣራ​ቸው ይፈ​ር​ሳል፤ ግድ​ግ​ዳ​ቸ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ይነ​ግ​ሣ​ልና፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ፊት ይከ​ብ​ራ​ልና።


ከእ​ና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ማን ነው? የባ​ሪ​ያ​ው​ንም ቃል ይስማ፤ በጨ​ለ​ማም የም​ት​ሄዱ፥ ብር​ሃ​ንም የሌ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ታመኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተደ​ገፉ፤


ምድ​ሪ​ቱን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ባዶ ነበ​ረች፤ ሰማ​ያ​ት​ንም ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ብር​ሃ​ንም አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።


በጠ​ፋ​ህም ጊዜ ሰማ​ዮ​ችን እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ ፀሐ​ዩ​ንም በደ​መና እሸ​ፍ​ና​ለሁ፤ ጨረ​ቃም ብር​ሃ​ኑን አይ​ሰ​ጥም።


የሰ​ማ​ይን ብር​ሃ​ኖች ሁሉ በላ​ይህ አጨ​ል​ማ​ለሁ፤ በም​ድ​ር​ህም ላይ ጨለ​ማን አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


በላይ በሰ​ማይ ድን​ቆ​ችን አሳ​ያ​ለሁ፤ በታች በም​ድ​ርም ደምና እሳት የጢ​ስም ጭጋግ።


ታላ​ቋና ግልጥ የሆ​ነ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።


ብር​ሃ​ንም በጨ​ለማ ያበ​ራል፤ ጨለ​ማም አላ​ገ​ኘ​ውም።


በእኔ የሚ​ያ​ምን ሁሉ በጨ​ለማ እን​ዳ​ይ​ኖር ብር​ሃን እኔ ወደ ዓለም መጣሁ።


ነገር ግን ይህ በነ​ቢዩ በኢ​ዩ​ኤል የተ​ባ​ለው ነው።


በላይ በሰ​ማይ ተአ​ም​ራ​ትን፥ በታች በም​ድ​ርም ምል​ክ​ቶ​ችን፥ ደምን እሳ​ት​ንና ጢስ​ንም እሰ​ጣ​ለሁ።


በብ​ር​ሃን ቅዱ​ሳን ለሚ​ታ​ደ​ሉት ርስት የበ​ቃን ያደ​ረ​ገ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።


ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios