Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘካርያስ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፣ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከግብጽ እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤ በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ። የሚበቃ ስፍራ እስኪጠባቸው ድረስ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከግብጽ ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦር እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታ እስኪጠባቸው ድረስ በገለዓድና በሊባኖስም ጭምር አሰፍራቸዋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም።

Ver Capítulo Cópia de




ዘካርያስ 10:10
16 Referências Cruzadas  

ታናሹ ሺህ፥ የሁ​ሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለ​ዓ​ድና እንደ ሊባ​ኖስ ራስ ነህ፤ በር​ግጥ ምድረ በዳና ማንም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው ከተ​ሞች አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ ማሰ​ማ​ር​ያው እመ​ል​ሳ​ለሁ፥ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስና በባ​ሳን፥ በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራና በገ​ለ​ዓ​ድም ይሰ​ማ​ራል፤ ነፍ​ሱም ትጠ​ግ​ባ​ለች።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እከ​ተ​ለው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ያድ​ነ​ና​ልና፤ እር​ሱም እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ የውኃ ልጆ​ችም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


እንደ ወፍ ከግ​ብፅ፥ እንደ ርግ​ብም ከአ​ሶር ምድር እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ይወ​ጣሉ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የጭ​ፍ​ራ​ቸው ምርኮ የከ​ነ​ዓ​ንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራ​ጵታ ድረስ ይወ​ር​ሳል፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምር​ኮ​ኞች እስከ ኤፍ​ራታ ድረስ የደ​ቡ​ብን ከተ​ሞች ይወ​ር​ሳሉ።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፣


አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios