Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሩት 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኑኃሚንም ምራትዋን ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው አለቻት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኑኃሚንም ምራቷን ሩትን፣ “የእኔ ልጅ፤ እንዲህ ካልሽማ ከሴት ሠራተኞቹ ጋራ ዐብሮ መሄድ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው አዝመራ ብትሄጂ ጕዳት ሊያገኝሽ ይችላልና” አለቻት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ናዖሚም ምራትዋን ሩትን፦ “ልጄ ሆይ፥ ከሴት አገልጋዮቹ ጋር ብትወጪ ይሻላል፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው” አለቻት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ናዖሚም “እውነት ነው ልጄ፤ በቦዔዝ እርሻ ካሉት ሴቶች ጋር ሆነሽ ብትቃርሚ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ብትሄጂ ግን ምናልባት ጐልማሶች ያስቸግሩሻል” አለቻት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሚኃሚንም ምራትዋን ሩትን “ልጄ ሆይ! ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው፤” አለቻት።

Ver Capítulo Cópia de




ሩት 2:22
5 Referências Cruzadas  

አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ያላ​ወ​ቅሽ እንደ ሆነ የመ​ን​ጎ​ችን ፍለጋ ተከ​ት​ለሽ ውጪ፥ የፍ​የል ግል​ገ​ሎ​ች​ሽ​ንም በእ​ረ​ኞች ድን​ኳ​ኖች አጠ​ገብ አሰ​ማሪ።


ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፤


ሞዓባዊቱ ሩትም፦ ደግሞ፦ መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ አለኝ አለቻት።


ሩትም የገብሱና የስንዴው መከር እስኪጨረስ ድረስ ልትቃርም የቦዔዝን ገረዶች ተጠጋች፣ በአማትዋም ዘንድ ትቀመጥ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios