Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሮሜ 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እን​ግ​ዲህ ምን ትላ​ለህ? አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትነ​ቅ​ፈ​ዋ​ለ​ህን? ምክ​ሩ​ንስ የሚ​ቃ​ወ​ማት አለን?።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሠናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንግዲህ “ታዲያ ለምን እስከ አሁን ስህተት ይፈልጋል? ፈቃዱን ሊቃወም ማን ይችላል?” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመቃወም ማንም አይችልም፤ ታዲያ፥ እርሱ ሰዎችን በክፉ ሥራቸው ለምን ይወቅሳቸዋል” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de




ሮሜ 9:19
19 Referências Cruzadas  

እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ሆይ፥ በሰ​ማይ ያለህ አም​ላክ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንስ መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የም​ት​ገዛ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? ኀይ​ልና ችሎታ በእ​ጅህ ነው፤ ሊቋ​ቋ​ም​ህም የሚ​ችል የለም።


እርሱ በኀ​ይል ይይ​ዛ​ልና፤ ፍር​ዱን ማን ይቃ​ወ​ማል?


እነሆ፥ ዛሬ ጀመ​ርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ርቅ።


ይህ የእ​ና​ንተ ጠማ​ም​ነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የም​ት​ቈ​ጠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በውኑ ሥራ ሠሪ​ውን፥ “አል​ሠ​ራ​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን? ወይስ የተ​ደ​ረገ አድ​ራ​ጊ​ውን፥ “በማ​ስ​ተ​ዋል አላ​ሳ​መ​ር​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን?


የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት! ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አላቸው።


እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።


ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ተሰ​በሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ “እኔ የዘ​ይት ቅር​ን​ጫፍ ሆንሁ” ትል ይሆ​ናል።


ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነ​ሥ​ቶ​አል ብለን ለሌ​ላው የም​ና​ስ​ተ​ምር ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ሙታን አይ​ነ​ሡም የሚሉ እን​ዴት ይኖ​ራሉ?


ሙታን እን​ዴት ይነ​ሣሉ? የሚ​ነ​ሡስ በምን አካ​ላ​ቸው ነው? የሚል አለ።


ማንም ሲፈተን “በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፤” አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።


ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ፤” ይላል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios