Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሮሜ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አብ​ር​ሃም የመቶ ዓመት ሽማ​ግሌ ስለ​ሆነ እንደ ምውት የሆ​ነ​ውን የራ​ሱን ሥጋና የሣራ ማኅ​ፀን ምውት መሆ​ኑን እያየ በእ​ም​ነት አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እርሱ የመቶ ዓመት ሰው ሆኖ ሳለ፣ የራሱም ሰውነት ሆነ የሣራ ማሕፀን ምዉት እንደ ነበረ እያወቀ በእምነቱ አልደከመም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 መቶ ዓመት ሆኖት ሳለ ምውት የሆነውን የራሱን አካልና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆን አስቦ በእምነት አልደከመም፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ዕድሜው መቶ ዓመት ያኽል ስለ ነበረ በሥጋው መድከም እንደ ሞተ በመሆን ምክንያት መውለድ እንደማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆንዋ መውለድ እንደማትችል ቢያውቅም በእምነቱ ደካማ አልሆነም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤

Ver Capítulo Cópia de




ሮሜ 4:19
11 Referências Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ዘጠና ዓመት የሆ​ና​ትም ሣራ ትወ​ል​ዳ​ለ​ችን?”


እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውሃው ላይ ሄደ።


ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፤ ስለምን ተጠራጠርህ?” አለው።


እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?


እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


ለወ​ን​ድም ዕን​ቅ​ፋት ከመ​ሆን ሥጋን አለ​መ​ብ​ላት ወይ​ን​ንም አለ​መ​ጠ​ጣት ይሻ​ላል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios