Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሮሜ 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ይኸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን በአ​ገ​ል​ግ​ሎቴ ደስ አሰ​ና​ቸው ዘንድ በይ​ሁዳ ሀገር ካሉ ዐላ​ው​ያን እን​ዲ​ያ​ድ​ነኝ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በይሁዳ ካሉት ከማያምኑት እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለው አገልግሎቴም በዚያ ባሉት ቅዱሳን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩልኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ይህም በይሁዳ ካሉት፥ ከማይታዘዙት እንድድን፥ ለኢየሩሳሌምም ያለኝ አገልግሎቴ በቅዱሳን ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የምትጸልዩልኝም በይሁዳ ምድር ካሉት ከማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለኝ አገልግሎትም በእግዚአብሔር ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31-32 በእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ወደ እናንተ መጥቼ ከእናንተ ጋር እንዳርፍ፥ በይሁዳ ካሉት ከማይታዘዙ እድን ዘንድ፥ ለኢየሩሳሌምም ያለኝ አገልግሎቴ ቅዱሳንን ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ ጸልዩ።

Ver Capítulo Cópia de




ሮሜ 15:31
18 Referências Cruzadas  

የሻ​ለ​ቃው የሚ​ጮ​ሁ​በት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር እን​ዲ​ያ​ገ​ቡ​ትና እየ​ገ​ረፉ የሠ​ራ​ውን እን​ዲ​መ​ረ​ም​ሩት አዘዘ።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሎ​ችም ከበ​ቡት፤ የጳ​ው​ሎ​ስ​ንም ነገር ነገ​ሩት።


ፊስ​ጦ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ እና​ን​ተም ከእኛ ጋር ያላ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ችሁ፥ ስሙ፤ አይ​ሁድ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እን​ዳ​ይ​ገ​ባው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆነ በዚህ እየ​ጮሁ የለ​መ​ኑኝ ይህ የም​ታ​ዩት ሰው እነሆ።


ሐና​ንያ ግን መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ ሰው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በቅ​ዱ​ሳ​ኖ​ችህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰም​ቻ​ለሁ።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና።


አሁን ግን ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እሄ​ዳ​ለሁ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስና የፈ​ር​ዶ​ና​ጥስ፥ የአ​ካ​ይ​ቆ​ስም ቤተ​ሰ​ቦች፥ የአ​ካ​ይያ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ለማ​ገ​ል​ገል ራሳ​ቸ​ውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ሆ​ነው አገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ተ​ባ​በሩ ይህን ቸር​ነት መላ​ል​ሰው ማለ​ዱን።


ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አገ​ል​ግ​ሎት የም​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ ብዙ አለኝ


ክር​ስ​ቶስ ላስ​ተ​ማ​ራት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና፥ ሁላ​ች​ሁም ደስ ብሎ​አ​ች​ሁና ተባ​ብ​ራ​ችሁ አወ​ጣ​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚች በሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ ፈተና ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤


እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ፤ ነቢያትንም እኛንም አሳደዱ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፤ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፤


ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios