Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 76:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በውኑ ይጥ​ላ​ልን? እን​ግ​ዲ​ህስ ይቅ​ር​ታ​ውን አይ​ጨ​ም​ር​ምን?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሁሉ ዘንድ የተፈራህ ነህ፤ አንተ ስትቈጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ አይኖርም፤

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 76:7
15 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ፥ ምስ​ጋ​ና​ውም ብዙ ነውና፤ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ የተ​ፈራ ነው።


አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አም​ል​ጠን ቀር​ተ​ናል፤ እነሆ በፊ​ትህ በበ​ደ​ላ​ችን አለን፤ ስለ​ዚህ በፊ​ትህ ሊቆም የሚ​ችል የለም።”


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እስ​ራ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይታ​መ​ናል።


ጥበ​ብን አጽ​ኑ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ እና​ን​ተም ከጽ​ድቅ መን​ገድ እን​ዳ​ት​ጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነ​ደ​ደች ጊዜ፥ በእ​ርሱ የታ​መኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።


በመ​ን​ገ​ድህ ሁሉ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ቱን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።


የፈ​ር​ዖ​ንን ሰረ​ገ​ሎች፥ ሠራ​ዊ​ቱ​ንም በባ​ሕር ጣላ​ቸው። በሦ​ስት የተ​ከ​ፈሉ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም በኤ​ር​ትራ ባሕር ሰጠሙ።


በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?


በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios