Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 68:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የሚመራቸው ትንሹ ብንያም ነው፤ በዚያ በብዙ የሚቈጠሩ የይሁዳ መሳፍንት፣ እንዲሁም የዛብሎንና የንፍታሌም መሳፍንት ይገኛሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እግዚአብሔርን በጉባኤ፥ የእስራኤል ምንጭ ጌታችንንም አመስግኑት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 68:27
17 Referências Cruzadas  

እኛ የአ​ባ​ታ​ችን ልጆች ዐሥራ ሁለት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነን፤ አንዱ ሞቶ​አል፤ ታና​ሹም በከ​ነ​ዓን ምድር ዛሬ ከአ​ባ​ታ​ችን ጋር አለ።


አበ​ኔ​ርም ደግሞ በብ​ን​ያም ልጆች ጆሮ ተና​ገረ፤ አበ​ኔ​ርም ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በብ​ን​ያም ቤት ሁሉ መል​ካም የነ​በ​ረ​ውን ለዳ​ዊት ሊነ​ግ​ረው ወደ ኬብ​ሮን ሄደ።


ዳዊ​ትም ወደ ነበ​ረ​ባት ወደ አን​ባ​ዪቱ ከብ​ን​ያ​ምና ከይ​ሁዳ ወገን ሰዎች ዳዊ​ትን ለመ​ር​ዳት መጡ።


የሳ​ኦ​ልም ወን​ድ​ሞች ከሆኑ ከብ​ን​ያም ልጆች ሦስት ሺህ ነበሩ። የሚ​በ​ል​ጠው ክፍል የሳ​ኦ​ልን ቤት ይጠ​ብቁ ነበሩ።


ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ዘጠ​ነ​ኛው አለቃ ከብ​ን​ያ​ማ​ው​ያን የነ​በ​ረው ዓና​ቶ​ታ​ዊው አቢ​ዔ​ዜር ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።


ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ፈቃድ አት​ስ​ጠኝ፥ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሐሰ​ትም የዐ​መፅ ራስ ነው።


አም​ላክ ሆይ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይቅ​ር​ታ​ህን ተቀ​በ​ልን።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ይቅ​ር​ታ​ው​ንና ጽድ​ቁን ማን ይፈ​ል​ጋል?


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ቅናት ይሻ​ራል፤ የይ​ሁ​ዳም ጠላ​ቶች ይጠ​ፋሉ፤ ኤፍ​ሬ​ምም በይ​ሁዳ አይ​ቀ​ናም፤ ይሁ​ዳም ኤፍ​ሬ​ምን አያ​ስ​ጨ​ን​ቅም።


እና​ንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ከይ​ሁ​ዳም የወ​ጣ​ችሁ፥ በእ​ው​ነት ሳይ​ሆን፥ በጽ​ድ​ቅም ሳይ​ሆን እር​ሱን እየ​ጠ​ራ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የም​ት​ምሉ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤


ከብ​ን​ያም ነገድ የኪ​ስ​ሎን ልጅ ኤል​ዳድ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ጣላ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ን​ያም ሃያ አም​ስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎ​ችን ገደሉ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ነበሩ።


ዛብ​ሎን ነፍ​ሱን ወደ ሞት ያሳ​ለፈ ሕዝብ ነው፤ ንፍ​ታ​ሌ​ምም በሀ​ገሩ ኮረ​ብታ ላይ ነው።


ሳኦ​ልም መልሶ፥ “እኔ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ከሚ​ያ​ንስ ወገን የሆ​ንሁ ብን​ያ​ማዊ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ወገ​ኔስ ከብ​ን​ያም ነገድ ወገ​ኖች ሁሉ የሚ​ያ​ንስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ዲ​ህስ ያለ​ውን ነገር ለምን ነገ​ር​ኸኝ?” አለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios