Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 34:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አፋ​ቸ​ው​ንም በእኔ ላይ አላ​ቀቁ፤ እሰይ፥ እሰይ፥ በዐ​ይ​ና​ችን አየ​ነው ይላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤ ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤ ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 34:21
22 Referências Cruzadas  

ወደ ሰማ​ር​ያም መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም በሰ​ማ​ርያ ቀበ​ሩት፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ የሚ​ባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መል​ካም አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ” አለው። የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሥ እን​ዲህ አይ​በል” አለ።


እጅህ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው፥ ቀኝ​ህም የሚ​ጠ​ሉ​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው።


በአ​ንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥ​ጋ​ውም አን​ዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታ​ውጡ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም አት​ስ​በሩ።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ሰባት ጊዜም ይነሣል። ኃጥኣን ግን በክፉ ደዌ ይያዛሉ።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።


ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”


ዓለም እና​ን​ተን ሊጠ​ላ​ችሁ አይ​ች​ልም፤ እኔን ግን ይጠ​ላ​ኛል፤ ሥራዉ ክፉ እንደ ሆነ እኔ እመ​ሰ​ክ​ር​በ​ታ​ለ​ሁና።


ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።


በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።


ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ወ​ጉ​ኝና እን​ዳ​ይ​ሳ​ለ​ቁ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios