Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 33:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ጻድ​ቃን ጮኹ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ​ቸው፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ አዳ​ና​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጕልበቱም ማንንም አያድንም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፥ በኃይሉም ብዛት አያስመልጥም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ፈረስ ለማዳን ከንቱ ተስፋ ነው፤ ከዚያ ሁሉ ኀይሉ ጋር ሊያድን አይችልም።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 33:17
12 Referências Cruzadas  

ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


እጅህ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው፥ ቀኝ​ህም የሚ​ጠ​ሉ​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው።


ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ረድኤት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


ነገር ግን፥ በፈ​ረስ ላይ ተቀ​ም​ጠን እን​ሸ​ሻ​ለን እንጂ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ደግ​ሞም በፈ​ጣን ፈረስ ላይ እን​ቀ​መ​ጣ​ለን አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ ፈጣ​ኖች ይሆ​ናሉ።


ርዳታ ለመ​ፈ​ለግ ወደ ግብፅ ለሚ​ወ​ርዱ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ለሚ​ታ​መኑ ወዮ​ላ​ቸው! ፈረ​ሰ​ኞቹ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ አል​ታ​መ​ኑ​ምና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ምና።


ከእ​ና​ንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለሱ። እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ኀጢ​አ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ግድ፤ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​በ​ለን፤ በወ​ይ​ፈ​ንም ፈንታ የከ​ን​ፈ​ራ​ች​ንን ፍሬ ለአ​ንተ እን​ሰ​ጣ​ለን።


“ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ሠራ​ዊ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ርቅ ፊት በሰ​ይፍ ስለት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ ሲሣ​ራም ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ በእ​ግሩ ሸሸ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios