Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 32:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ምክር ይመ​ል​ሳል፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ዐሳብ ይመ​ል​ሳል። የአ​ለ​ቆ​ችን ምክ​ራ​ቸ​ውን ያስ​ረ​ሳ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የክፉዎች ዋይታ ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን፣ ምሕረት ይከብበዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በኃጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት፥ በጌታ የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከብበዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የኃጢአተኞች መከራ ብዙ ነው። በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሩ ይሸፍናቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 32:10
20 Referências Cruzadas  

በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ኀይ​ሉም ታላቅ ነው፥ ለጥ​በ​ቡም ቍጥር የለ​ውም።


የሰ​ውን ሥራ አፌ እን​ዳ​ይ​ና​ገር፥ ስለ ከን​ፈ​ሮ​ችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መን​ገ​ዶ​ችን ጠበ​ቅሁ።


ጥበ​ብን አጽ​ኑ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ እና​ን​ተም ከጽ​ድቅ መን​ገድ እን​ዳ​ት​ጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነ​ደ​ደች ጊዜ፥ በእ​ርሱ የታ​መኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


ያላ​ወ​ቋት ወጥ​መድ ትም​ጣ​ባ​ቸው፥ የሸ​ሸ​ጓ​ትም ወጥ​መድ ትያ​ዛ​ቸው፤ በዚ​ህ​ችም ወጥ​መድ ውስጥ ይው​ደቁ።


እኔስ፥ “አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አን​ተን በድ​ያ​ለ​ሁና ለነ​ፍሴ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላት” አልሁ።


አንተ ጻድ​ቁን ትባ​ር​ከ​ዋ​ለ​ህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላ​ባሽ ጋሻ ከለ​ል​ኸን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱን ይሰ​ጣል፥ ምድ​ርም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች።


በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


በሥራ ዐዋቂ የሆነ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔርም የታመነ ብፁዕ ነው።


የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


ለኃ​ጥ​አን ደስታ የላ​ቸ​ውም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios