Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 106:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እር​ሻ​ዎ​ች​ንም ዘሩ፥ ወይ​ኖ​ች​ንም ተከሉ፥ የእ​ህ​ል​ንም ሰብል አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንትና በከነዓን አገር ለሚገኙ ጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 106:37
19 Referências Cruzadas  

ነገር ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ልጁን በእ​ሳት ሠዋው።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


እርሱ ግን ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ ከንቱ ለሆኑ ጣዖ​ታ​ቱም፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ለሠ​ራ​ቸው እን​ቦ​ሶ​ችም ካህ​ና​ትን አቆመ።


እና​ንተ በለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣ​ዖት ደስ የም​ት​ሰኙ፥ እና​ን​ተም በሸ​ለ​ቆች ውስጥ በዓ​ለ​ትም ስን​ጣ​ቂ​ዎች በታች ልጆ​ቻ​ች​ሁን የም​ት​ሠዉ፥ እና​ንተ የጥ​ፋት ልጆ​ችና የዐ​መ​ፀ​ኞች ዘሮች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?


ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”


እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ያለ​ች​ውን የቶ​ፌ​ትን መሥ​ዊ​ያ​ዎች ሠር​ተ​ዋል።


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ እን​ዲ​ያ​ውቁ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ማኅ​ፀን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ በአ​መ​ጡ​ልኝ ጊዜ፥ በመ​ባ​ቸው አረ​ከ​ስ​ኋ​ቸው።


ቍር​ባ​ና​ች​ሁን በአ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም በእ​ሳት ባሳ​ለ​ፋ​ችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ሳ​ባ​ችሁ ሁሉ ረከ​ሳ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ደምም በእ​ጃ​ቸው አለና፥ ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንም ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ ለእ​ኔም የወ​ለ​ዱ​አ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን መብል እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው በእ​ሳት አሳ​ል​ፈ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።


ጉባ​ኤ​ውም በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፋ​ቸ​ውም ይቈ​ር​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይገ​ድ​ላሉ፤ ቤቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”


ከዘ​ር​ህም ለሞ​ሎክ አት​ስጥ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ስም አታ​ር​ክስ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?


አሕ​ዛ​ብም የሚ​ሠዉ ለአ​ጋ​ን​ንት ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የአ​ጋ​ን​ንት ተባ​ባ​ሪ​ዎች እን​ድ​ት​ሆኑ አል​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ች​ሁም።


ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእ​ሳት የሚ​ሠዋ፥ ምዋ​ር​ተ​ኛም፥ ሞራ ገላ​ጭም፥ አስ​ማ​ተ​ኛም፥ መተ​ተ​ኛም፥


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለአ​ጋ​ን​ንት፥ ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ውም አማ​ል​ክት፥ ድን​ገት ለተ​ገኙ ለማ​ይ​ሠ​ሩና ለማ​ይ​ጠ​ቅሙ አማ​ል​ክት፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው አማ​ል​ክት ሠዉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios