Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 103:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የአ​ን​በ​ሶች ግል​ገ​ሎች ያገ​ሣሉ፥ ይነ​ጥ​ቃ​ሉም፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሻሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፣ ሰራዊቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፥ ጌታን ባርኩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አገልጋዮቹ የሆናችሁ፥ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ፥ እናንተ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን አመስግኑ!

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 103:21
16 Referências Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም በአ​ያ​ቸው ጊዜ፥ “እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ናቸው” አለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ተዓ​ይን” ብሎ ጠራው።


ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።


ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው፤ ቆመው አየሁ።”


ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ልብ ደስ ይበ​ለው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ትጸ​ና​ላ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊዜ ፊቱን ፈልጉ።


ይህ ችግ​ረኛ ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፥ ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው።


ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።


የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፤


ድን​ገ​ትም ከዚያ መል​አክ ጋር ብዙ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ መጡ።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios