Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 23:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ወደ እርሷ የሄደ ፈጥኖ ይጠፋል፥ ጠማማ ሰውም ሁሉ ያልቃል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እንደ ወንበዴ ታደባለች፤ በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንደ ሌባ ታደባለች የእምነተቢሶችንም ቍጥር ታበዛለች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እንደ ወንበዴ አድብተው ይጠብቁሃል፤ ብዙ ወንዶችን በሕጋዊ ጋብቻ ታማኝ ሆነው እንዳይኖሩ አድርገዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 23:28
15 Referências Cruzadas  

ይህ​ንም ነገር በየ​ዕ​ለቱ ለዮ​ሴፍ ትነ​ግ​ረው ነበር፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይሆን ዘንድ አል​ሰ​ማ​ትም።


የዐመፀኛ አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተጠላ በእርሱ ውስጥ ይወድቃል። በሰው ፊት ክፉዎች መንገዶች አሉ፥ ከእነርሱም ይርቅ ዘንድ አይወድድም። ከክፉና ከጠማማ መንገድም መራቅ አግባብ ነው።


የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።


የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።


አንድ ጊዜ በጎዳና፥ በሌላ ጊዜም በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።


ነገር ግን እርሱ ከኀያላን ወገን በእርሷ ዘንድ የሚጠፉ እንዳሉ፥ የሲኦል ወጥመድም በቤቷ እንደሚገኝ አያውቅም። ነገር ግን ፈጥነህ ሂድ፥ በቦታዋም አትዘግይ፥ የባዕድን ውኃ እንደምትሻገር በዐይንህ ወደ እርሷ መመልከትን አታዘውትር። ከባዕድ ውኃ ራቅ፥ ብዙ ዘመን ትኖር ዘንድ ከባዕድ ምንጭ ውኃ አትጠጣ። የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።


እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን አቅ​ን​ተሽ አንሺ፤ ያል​ተ​ጋ​ደ​ም​ሽ​በት ስፍራ እን​ዳ​ለም ተመ​ል​ከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራ​ዎች በመ​ን​ገድ ላይ ተቀ​ም​ጠሽ በዝ​ሙ​ት​ሽና በክ​ፋ​ትሽ ምድ​ሪ​ቱን አር​ክ​ሰ​ሻ​ታ​ልና።


የሕ​ዝቤ ልቡ​ና​ቸው ዝሙ​ትን፥ መጠ​ጥ​ንና ስካ​ርን ወደደ።


እስ​ራ​ኤ​ልም በሰ​ጢን አደሩ፤ ሕዝ​ቡም ከሞ​ዓብ ልጆች ጋር አመ​ነ​ዘሩ፤ ረከ​ሱም።


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ ሴሰኑ፥ በአ​ንድ ቀንም ሃያ ሦስት ሺህ ሰዎች እንደ ወደቁ አን​ሴ​ስን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios