Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 22:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ራሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ይርቃል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 22:5
15 Referências Cruzadas  

እግሩ በወ​ጥ​መድ ትያ​ዛ​ለች፤ በመ​ረ​ብም ትታ​ሠ​ራ​ለች፤


በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤


መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን ይሰጣል፤ የቸለልተኞች መንገድ ግን በጥፋት ውስጥ ነው።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።


የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ የጽኑዓን መንገዶች ግን ጥርጊያ ናቸው።


የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።


ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።


እግዚአብሔርን መፍራት፥ ጥበብን ባለጠግነትንና ክብርን፥ ሕይወትንም ትወልዳለች።


የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው። እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ክ​ት​ጠፉ ድረስ መው​ደ​ቂ​ያና ወጥ​መድ፥ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ችን​ካር፥ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም እሾህ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል እንጂ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ችሁ ዕወቁ።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios