Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤ ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ስለዚህ መልካም ምክር ሳትቀበል ወደ ጦርነት አትሂድ።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 20:18
16 Referências Cruzadas  

አሁ​ንም ነዪ፤ የል​ጅ​ሽን የሰ​ሎ​ሞ​ንን ነፍ​ስና የአ​ን​ቺን ነፍስ እን​ድ​ታ​ድኚ እመ​ክ​ር​ሻ​ለሁ።


የከ​ን​ፈር ቃል ለሰ​ልፍ ምክ​ርና ኀይል እን​ደ​ሚ​ሆን ትና​ገ​ራ​ለህ፤ አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው?


መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።


ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። ምክርም በመካሮች ልብ ትኖራለች።


በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ ርዳታም ከምትመክር ልብ ጋር ይሆናል።


ንጉ​ሥም ሌላ​ውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ሊሄድ ቢወድ ሁለት እልፍ ይዞ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ውን በአ​ንድ እልፍ ሊዋ​ጋው ይችል እንደ ሆነ አስ​ቀ​ድሞ ተቀ​ምጦ ይመ​ክር የለ​ምን?


ከዚ​ያም በኋላ ያያት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲህ ያለ ነገር የሆ​ነ​በት ጊዜ የለም፤ የታ​የ​በ​ትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነ​ዚ​ያን የላ​ካ​ቸ​ውን ሰዎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች እን​ዲህ በሏ​ቸው፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እን​ዲህ የሆ​ነ​በት ጊዜ አለን? እና​ንተ ተመ​ካ​ከ​ሩ​በት፤ የሚ​በ​ጀ​ው​ንም ተነ​ጋ​ገሩ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።


እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላ​ችሁ፥ ምክ​ራ​ች​ሁ​ንና እዝ​ና​ታ​ች​ሁን በዚህ ስጡ።”


ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤ​ሜ​ሌ​ክን አሳ​ድ​ደው ነበር” አለ። አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም፥ “ሠራ​ዊ​ት​ህን አብ​ዝ​ተህ ና፤ ውጣ” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios