Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ደግ ነገር ተደርጎለት ክፉ ነገር የሚመልስ ክፉ ነገር ዘወትር ከቤቱ አይለይም።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 17:13
18 Referências Cruzadas  

ስለ​ዚ​ህም አቃ​ል​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥ የኬ​ጤ​ያ​ዊ​ው​ንም የኦ​ር​ዮን ሚስት ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃ​ልና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከቤ​ትህ ሰይፍ አይ​ር​ቅም።


አንድ ነቢ​ይም ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚ​መ​ጣው ዓመት ይመ​ጣ​ብ​ሃ​ልና፥ በርታ፤ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ዕወቅ” አለው።


ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ በዚያ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ይሰ​ደ​ዳሉ፥ መቆ​ምም አይ​ች​ሉም።


በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።


ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።


ክፉ ላደ​ረ​ገ​ባ​ች​ሁም ክፉ አት​መ​ል​ሱ​ለት፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ​ውን ተነ​ጋ​ገሩ።


ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።


ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።


ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል ስለ ዳዊት መል​ካም ተና​ገረ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እርሱ አል​በ​ደ​ለ​ህ​ምና፥ ሥራ​ውም ለአ​ንተ እጅግ መል​ካም ሆኖ​አ​ልና ንጉሡ ባሪ​ያ​ውን ዳዊ​ትን አይ​በ​ድ​ለው፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።


ዳዊ​ትም አለ፥ “ለዚህ ሰው ከሆ​ነው ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​በት በእ​ው​ነት ከብ​ቱን ሁሉ በም​ድረ በዳ በከ​ንቱ ጠበ​ቅሁ፤ ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ አን​ዳች ይወ​ስ​ዱ​በት ዘንድ ያዘ​ዝ​ነው የለም፤ እር​ሱም በበጎ ፋንታ ክፉ መለ​ሰ​ልኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios