Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን የሚናገረው ሐሰት ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 14:5
15 Referências Cruzadas  

እነ​ሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ አክ​ዓብ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያ​ለ​ህን? እነሆ፥ ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።


“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ላይ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር።


“ሐሰ​ተኛ ወሬ አት​ቀ​በል፤ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ርም ትሆን ዘንድ ከዐ​መ​ፀኛ ጋር አት​ቀ​መጥ።


ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው።


ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም።


እውነተኛ ምስክር ነፍስን ከክፉ ያድናል፥ ሐሰተኛ ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።


በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።


በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።


ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።


ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አይድንም፤ ክፋትን የሚያቀጣጥላትም ይጠፋባታል።


ሐሰተኛ ምስክርን የሚያቀጣጥል፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።


በዐ​መፃ ይከ​ስ​ሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰ​ተኛ ምስ​ክር ቢቆም፥


“በሎዲቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios