Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ተግሣጽ የሕይወትን መንገድ ይጠብቃታል፤ በተግሣጽ የማይዘለፍ ግን ይስታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤ ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፥ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ተግሣጽን የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ያመራሉ፤ ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰዎች ግን አደጋ ላይ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 10:17
22 Referências Cruzadas  

እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ንጉሡ አሜ​ስ​ያስ፥ “በውኑ የን​ጉሡ አማ​ካሪ ልት​ሆን ሹሜ​ሃ​ለ​ሁን? ቅጣት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። ነቢ​ዩም፥ “ይህን አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ ምክ​ሬ​ንም አል​ሰ​ማ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋህ እን​ዳ​ሰበ አወ​ቅሁ” ብሎ ዝም አለ።


ምክሬን ይመለከቱ ዘንድ አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤


ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው።


የቅኖች ትምህርት በሚያልፉ ሰዎች ትታወቃለች። ተግሣጽን የሚጠሉ ግን በውርደት ይሞታሉ።


ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል። ተግሣጽን የሚወድድ ግን ራሱን ይወድዳል።


እርስዋ ለሚመረኰዛት ሁሉ የሕይወት ዛፍ ናት፥ የሚታመኑባትም በእግዚአብሔር እንደ ጸና ሰው ናቸው።


ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።


ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦ ቃላችን በልብህ ይኑር፤ ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም።


እንዲህም ትላለህ፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ! ልቤም ከተግሣጽ እንዴት ራቀ!


በማኅበርና በጉባኤ መካከል፥ ወደ ክፉ ሁሉ ለመድረስ ጥቂት ቀረኝ።”


ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ ትምህርትና ተግሣጽም የሕይወት መንገድ ነውና፥


ለሥ​ጋህ በደል አፍ​ህን አት​ስጥ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት፥ “ባለ​ማ​ወቅ ነው” አት​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ቃልህ እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ብህ፤


እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።


ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?


ስለ​ዚ​ህም ከሰ​ማ​ነው ነገር ምን​አ​ል​ባት እን​ዳ​ን​ወ​ሰድ ለእ​ርሱ አብ​ዝ​ተን ልን​ጠ​ነ​ቀቅ ይገ​ባ​ናል።


ዐይ​ኑ​ንም አን​ሥቶ መን​ገ​ደ​ኛ​ውን በከ​ተ​ማው አደ​ባ​ባይ አየ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ውም፥ “ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ?” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios