Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የባለጠጋ ሀብት የጸናች ከተማ ናት፤ የዕውቀት ድህነት ግን የኀጢአተኞች ጥፋት ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የሀብታም መዝገቡ የጸናች ከተማ ናት፥ የድሆች ውድቀት ድህነታቸው ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ባለጸጋን ሀብቱ እንደ ምሽግ ሆኖ ይጠብቀዋል፤ ድኻውን ግን ድኽነቱ ያጠፋዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 10:15
13 Referências Cruzadas  

ሰማ​ያት ጽድ​ቁን ይና​ገ​ራሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና።


ባለጠጎች ወዳጆች ድሆች ወዳጆችን ይጠላሉ፤ የባለጠጎች ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።


የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥ ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።


ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።


የጥ​በብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻ​ላል፤ የጥ​በ​ብ​ንም ዕው​ቀት ማብ​ዛት ገን​ዘብ ላደ​ረ​ጋት ሕይ​ወ​ትን ትሰ​ጠ​ዋ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ። ኢየሱስም ደግሞ መልሶ “ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው።


ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዲህ እላ​ታ​ለሁ፦ ሰው​ነቴ ሆይ፥ የሰ​በ​ሰ​ብ​ሁ​ልሽ ለብዙ ዓመ​ታት የሚ​በ​ቃሽ የደ​ለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበ​ልሽ።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios