Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 1:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፥ ከክፉም ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያርፋል።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 የሚሰማኝ ግን ተረጋግቶ ይቀመጣል፥ ከክፉም ሥጋት ያርፋል።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እኔን የሚሰማ ግን ለሕይወቱ ዋስትና ይኖረዋል፤ ምንም የሚያስፈራው ነገር ሳይደርስበት በሰላም ይኖራል።”

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 1:33
22 Referências Cruzadas  

ቢሰ​ሙና ቢያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም፥ ዕድ​ሜ​አ​ቸ​ውን በመ​ል​ካም፥ ዘመ​ና​ቸ​ው​ንም በተ​ድላ ይፈ​ጽ​ማሉ።


ጻድቅን ምንም ክፉ ነገር ደስ አያሰኘውም፤ ክፉዎች ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።


እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያን ይተዋል።


በዚህ ሥርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ፥ የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።


የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤


በአ​ንተ ላይ ታም​ና​ለ​ችና በአ​ንተ የም​ት​ደ​ገፍ ነፍ​ስን ፈጽ​መህ በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ታ​ለህ።


የጽ​ድ​ቅም ሥራ ሰላም ይሆ​ናል፤ ጽድ​ቅም የዕ​ረ​ፍት ቦታን ይይ​ዛል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይታ​መ​ኑ​በ​ታል።


ትእ​ዛ​ዜን ብት​ሰማ ኖሮ፥ ሰላ​ምህ እንደ ወንዝ ጽድ​ቅ​ህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“ሥር​ዐ​ቴ​ንም አድ​ርጉ፤ ፍር​ዴ​ንም ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ውስጥ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ግ​ቡም ድረስ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


በት​ዕ​ግ​ሥ​ታ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን ገን​ዘብ ታደ​ር​ጓ​ታ​ላ​ችሁ።


ጦር​ነ​ት​ንና ጠብን፥ ክር​ክ​ር​ንም በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ አት​ደ​ን​ግጡ፤ አስ​ቀ​ድሞ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፤ ነገር ግን ወዲ​ያው የሚ​ፈ​ጸም አይ​ደ​ለም።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios