Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ፊልጵስዩስ 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ነገር ግን ምን አለ? በየ​ም​ክ​ን​ያቱ በእ​ው​ነ​ትም ቢሆን፥ በሐ​ሰ​ትም ቢሆን፥ ስለ ክር​ስ​ቶስ ይና​ገ​ራሉ፤ ሰው​ንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠ​ራሉ፤ በዚ​ህም ደስ ብሎ​ኛል፤ ወደ​ፊ​ትም ደስ ይለ​ኛል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ታዲያ ችግሩ ከምኑ ላይ ነው? ቁም ነገሩ በእውነትም ሆነ በማስመሰል በማንኛውም መንገድ ክርስቶስ መሰበኩ ነው። በዚህም ደስ ይለኛል። አዎን፤ ደስ ይለኛል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዳሩ ግን ይህ አድራጎታቸው ግድ የሚል ምን ነገር አለው? ብቻ በማመካኘትም ሆነ በእውነት በሁሉ መንገድ ክርስቶስ ይሰበክ እንጂ፤ ስለ ሆነም እኔ በዚህ ደስ ብሎኛል። ወደፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ያም ሆነ ይህ በዚህ ደስ ይለኛል፤ በማስመሰልም ሆነ በእውነት በሁሉም መንገድ ክርስቶስ ይሰበካል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል።

Ver Capítulo Cópia de




ፊልጵስዩስ 1:18
13 Referências Cruzadas  

“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


የመበለቶችን ቤት የሚበሉ፤ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”


እነ​ርሱ ግን ይህን ነገር አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ እን​ዳ​ይ​መ​ረ​ም​ሩት ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነውና፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም እን​ዳ​ይ​ጠ​ይ​ቁት ይፈ​ሩት ነበ​ርና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አት​ከ​ል​ክ​ሉት፤ ባለ​ጋ​ራ​ችሁ ካል​ሆነ ባል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ነውና” አላ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ከእ​ነ​ርሱ እን​በ​ል​ጣ​ለን? አይ​ደ​ለም፤ አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ንም፥ አረ​ማ​ዊ​ንም እነሆ፥ አስ​ቀ​ድ​መን ነቅ​ፈ​ና​ቸ​ዋል፤ ሁሉም ስተ​ዋ​ልና።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? የኦ​ሪ​ትን ሕግ ከመ​ሥ​ራት ወጥ​ተን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ስለ ገባን ኀጢ​አት እን​ሥ​ራን? አይ​ደ​ለም።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ሠዋ መሥ​ዋ​ዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከንቱ ናቸው።


እን​ግ​ዲህ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ በመ​ን​ፈስ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈሴ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እዘ​ም​ራ​ለሁ።


አሁ​ንም እኔም ብሆን፥ እነ​ር​ሱም ቢሆኑ እን​ዲህ እና​ስ​ተ​ም​ራ​ለን፤ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አም​ና​ች​ኋል።


እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios