Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ፊልጵስዩስ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ ክር​ስ​ቶስ ስም መታ​ሰ​ሬም በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉና በሰው ሁሉ ዘንድ ታው​ቆ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚህ የተነሣ እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንደ ሆነ፣ በቤተ መንግሥት ዘበኞችና በሌሎችም ሁሉ ዘንድ ታውቋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህም እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንደሆነ በክብር ዘበኞች ሁሉና በሌሎች ሁሉ ዘንድ ተገልጦአል፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እኔም የታሰርኩት በክርስቶስ ምክንያት መሆኑን የቤተ መንግሥት ዘበኞችና ሌሎችም እዚያ ያሉት ሰዎች ሁሉ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህም እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንዲሆን በንጉሥ ዘበኞች ሁሉና በሌሎች ሁሉ ዘንድ ተገልጦአል፥

Ver Capítulo Cópia de




ፊልጵስዩስ 1:13
17 Referências Cruzadas  

ጳው​ሎ​ስም፥ “በጥ​ቂ​ትም ቢሆን፥ በብ​ዙም ቢሆን አንተ ብቻ ሳት​ሆን ዛሬ የሚ​ሰ​ሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ ከእ​ስ​ራቴ በቀር እንደ እኔ እን​ዲ​ሆኑ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ።”


ለብ​ቻ​ቸ​ውም ገለል ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ብለው ተነ​ጋ​ገሩ፥ “ይህ ሰው እን​ዲ​ሞት ወይም እን​ዲ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ የሠ​ራው በደል የለም።”


ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጳው​ሎስ የአ​ይ​ሁ​ድን ታላ​ላቅ ሰዎች ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ቢሆን፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ታሰ​ርሁ ለሮም ሰዎች አሳ​ል​ፈው ሰጡኝ።


ስለ​ዚ​ህም ላያ​ችሁ፥ ልነ​ግ​ራ​ች​ሁና ላስ​ረ​ዳ​ችሁ ወደ እኔ እን​ድ​ት​መጡ ማለ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ስለ እስ​ራ​ኤል ተስፋ በዚህ ሰን​ሰ​ለት ታስ​ሬ​አ​ለ​ሁና።”


ጳው​ሎ​ስም በገ​ን​ዘቡ በተ​ከ​ራ​የው ቤት ሁለት ዓመት ተቀ​መጠ፤ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​በል ነበር።


ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ሆይ ስለ እና​ንተ እኔ ጳው​ሎስ የክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረ​ኛው ነኝ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ለተ​ጠ​ራ​ሁ​ላት አጠ​ራር በሚ​ገባ ትኖሩ ዘንድ በክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረኛ የሆ​ንሁ እኔ ጳው​ሎስ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ ወን​ጌ​ልም በእ​ስ​ራት መል​እ​ክ​ተኛ የሆ​ንሁ፦ መና​ገር እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ ስለ እርሱ በግ​ልጥ እና​ገር ዘንድ ጸልዩ።


እን​ዲ​ሁም እኔን እን​ዳ​ያ​ች​ሁኝ፥ የእ​ኔ​ንም ነገር እንደ ሰማ​ችሁ ምን​ጊ​ዜም ተጋ​ደሉ።


ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና።


ቅዱ​ሳ​ንም ሁሉ፥ ይል​ቁ​ንም ከቄ​ሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።


ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios