Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ፊልጵስዩስ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ይህ የደ​ረ​ሰ​ብኝ በእ​ው​ነት ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ፋ​ፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አሁንም ወንድሞች ሆይ፣ በእኔ ላይ የደረሰው ነገር ወንጌል በይበልጥ እንዲስፋፋ መርዳቱን ታውቁ ዘንድ እወድዳለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ይህ የደረሰብኝ በእውነት ወንጌልን ለማስፋፋት እንደሆነ እንድታውቁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወንድሞቼ ሆይ! በእኔ ላይ የደረሰው ነገር ሁሉ ወንጌል በይበልጥ እንዲስፋፋ ማድረጉን እንድታውቁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህ የደረሰብኝ በእውነት ወንጌልን ለማስፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ፊልጵስዩስ 1:12
19 Referências Cruzadas  

እነሆ፥ ዛሬ ጀመ​ርሁ አልሁ፥ ልዑል ቀኙን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ርቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያን ከሚ​መ​ኩ​ባ​ቸ​ውና ከሚ​ገ​ዙ​ላ​ቸው አማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


ይህም በእ​ነ​ርሱ ላይ ምስ​ክር ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል።


የተ​በ​ተ​ኑት ግን እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፥ አስ​ተ​ማ​ሩም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ከእኔ ጋር አንድ በመ​ሆ​ና​ችሁ፥


ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና።


ልጅ አባ​ቱን እን​ደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግል፥ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት እንደ አገ​ለ​ገ​ለኝ፥ የዚ​ህን ሰው ጠባ​ዩን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


እና​ንተ የፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትም​ህ​ርት ከመ​ቄ​ዶ​ንያ ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ከእ​ና​ንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በመ​ስ​ጠ​ትም ቢሆን፥ በመ​ቀ​በል ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ተ​ባ​በሩ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና።


እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።


ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios