Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




አብድዩ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤ መልእክተኛው ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህ ብሏል፤ “ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የአብድዩ ራእይ። ጌታ አምላክ ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከጌታ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በጦርነት እንነሣ ብሏል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አብድዩ ያየው ራእይ፦ እግዚአብሔር አምላክ ኤዶምን በተመለከተ አብድዩን ልኮአል፤ የሰማነውም የእግዚአብሔር መልእክት፦ “እኔ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ አደጋ እንዲጥሉ በማዘዝ ወደ ሕዝቦች መልእክተኛ ልኬአለሁ!” የሚል ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምተናል፥ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በሰልፍ እንነሣ ብሎአል።

Ver Capítulo Cópia de




አብድዩ 1:1
28 Referências Cruzadas  

ዔሳ​ውም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ከም​ስር ንፍ​ሮህ አብ​ላኝ፤ እኔ እጅግ ደክ​ሜ​አ​ለ​ሁና” አለው፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙ ኤዶም ተባለ።


ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።


በሴ​ይር ተራራ የሚ​ኖሩ የኤ​ዶ​ማ​ው​ያን አባት የዔ​ሳው ትው​ል​ድም እን​ዲህ ነው።


በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የተ​ነ​ገረ ነገር። አንዱ ከሴ​ይር፥ “ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?” ብሎ ጠራኝ።


ጕበ​ኛ​ውም፥ “ይነ​ጋል፤ ደግ​ሞም ይመ​ሻል፤ ትጠ​ይቁ ዘንድ ብት​ወ​ድዱ ጠይቁ፤ ተመ​ል​ሳ​ች​ሁም ኑ፥” አለ።


አለ​ቆች ምንም በጣ​ኔ​ዎስ ቢሆኑ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደ​ርሱ፥


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ጽዋ​ውን ወሰ​ድሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እኔን የላ​ከ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።


ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፤


በም​ድ​ርም ከሚ​ሰማ ወሬ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ ልባ​ች​ሁም የዛለ አይ​ሁን፤ በአ​ንድ ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ በሌ​ላው ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ በም​ድ​ርም ላይ ግፍ ይነ​ግ​ሣል፤ አለ​ቃም በአ​ለቃ ላይ ይነ​ሣል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


በሀ​ገ​ራ​ቸው ንጹ​ሑን ደም አፍ​ስ​ሰ​ዋ​ልና በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደ​ረ​ጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስም በረሃ ይሆ​ናል።


ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፥ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፥ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።


ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።


ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios