Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 32:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እር​ሱን ትታ​ች​ሁ​ታ​ልና ዳግ​መ​ኛም በም​ድረ በዳ ትታ​ች​ሁ​ታል፤ በዚ​ችም ማኅ​በር ሁሉ ላይ ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱን ከመከተል ብትመለሱ አሁንም ይህን ሁሉ ሕዝብ በምድረ በዳ ይተወዋል፤ ለሚደርስበትም ጥፋት ምክንያቱ እናንተው ትሆናላችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እርሱን ከመከተል ብትመለሱ እርሱ ዳግመኛ ሕዝቡን በምድረ በዳ ይተዋል፤ ይህንንም ሕዝብ ሁሉ ታጠፋላችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እናንተ የሮቤልና የጋድ ሰዎች አሁን እግዚአብሔርን ለመከተል እምቢ ብትሉ፥ እርሱም ይህን ሕዝብ እንደገና በምድረ በዳ ይተወዋል፤ በእነርሱም ላይ በሚደርሰው ጥፋት እናንተ ኀላፊዎች ትሆናላችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርሱን ከመከተል ብትመለሱ እርሱ ሕዝቡን በምድረ በዳ ደግሞ ይተዋል፤ ይህንንም ሕዝብ ሁሉ ታጠፋላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 32:15
14 Referências Cruzadas  

እር​ሱም ንጉ​ሡን አሳን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የብ​ን​ያ​ምን ሕዝብ ሁሉ ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አሳ ይሁ​ዳና ብን​ያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ብት​ሆኑ እርሱ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ብት​ፈ​ል​ጉ​ትም ይገ​ኝ​ላ​ች​ኋል፤ ብት​ተ​ዉት ግን ይተ​ዋ​ች​ኋል።


ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ሁሉ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ያወ​ጣሉ፤ አን​ተም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትያ​ዛ​ለህ እንጂ ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት ትቃ​ጠ​ላ​ለች።”


ወደ እር​ሱም ቀር​በው አሉት፥ “በዚህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ችን በረ​ቶ​ችን፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ንም ከተ​ሞ​ችን እን​ሠ​ራ​ለን፤


“ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፤ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት!


በመ​ብል ምክ​ን​ያት ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ታ​ሳ​ዝን ከሆ​ንህ ፍቅር የለ​ህም፤ በውኑ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ሰው በመ​ብል ምክ​ን​ያት ሊጐዳ ይገ​ባ​ልን?


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios