Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 28:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር ይቀርባል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለጌታም ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በየቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የመጠጥ መባ በመጨመር አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ለእግዚአብሔርም ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 28:15
14 Referências Cruzadas  

የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት።


“ስለ ሕዝ​ቡም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ያር​ዳል፤ ደሙ​ንም ወደ መጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም ደም እን​ዳ​ደ​ረገ በፍ​የሉ ደም ያደ​ር​ጋል፤ በመ​ክ​ደ​ኛው ላይና በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት ይረ​ጨ​ዋል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርኩ​ስ​ነት፥ ከመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም፥ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለመ​ቅ​ደሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው መካ​ከል ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለኖ​ረች ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ያደ​ር​ጋል።


የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ከፍ​የ​ሎች ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያቀ​ር​ባል፤


በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት ያል​ታ​ወቀ ኀጢ​አት ቢኖር፥ ማኅ​በሩ ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ንጹሕ ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባሉ። የእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና የመ​ጠጡ ቍር​ባ​ንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀ​ር​ባሉ።


የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ይህ ነው፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ዕለት ዕለት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።


ማስ​ተ​ስ​ረ​ያም የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios