Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 22:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፣ “መሄዱን ከሰዎቹ ጋራ ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው። ስለዚህ በለዓም ከባላቅ አለቆች ጋራ ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የጌታም መልአክ በለዓምን፦ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ” አለው። በለዓምም ከባላቅ ሹማምንት ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 መልአኩ ግን “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄዱን ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው፤ በዚህ ዐይነት በለዓም ከባላቅ ባለሥልጣኖች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፦ ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 22:35
8 Referências Cruzadas  

ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አም​ላኬ የሚ​ለ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


“ባላ​ቅም በለ​ዓም እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ከዳ​ር​ቻ​ዎች በአ​ን​ደኛ ክፍል በአ​ለ​ችው በአ​ር​ኖን ዳርቻ ወደ አለ​ችው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊገ​ና​ኘው ወጣ።


እኔ ግን ላጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ መባ​ረ​ክ​ንም ባረ​ክ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ጁም አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios