Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 2:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ እን​ዲሁ በየ​ዓ​ላ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ሰፈሩ፤ እን​ዲ​ሁም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ተጓዙ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች እየሆኑ ተጓዙ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በዚህ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤ እያንዳንዱ ነገድ ዓርማውን በመከተል ይሰፍር ነበር፤ እያንዳንዱም በየቤተሰቡ ተመድቦ ይጓዝ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 2:34
15 Referências Cruzadas  

ሰላ​ምን ከሚ​ጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገ​ሠች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥራ​ውን ሁሉ ሠሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በሲና ምድረ በዳ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በየ​ሰ​ፈሩ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው በየ​አ​ለ​ቃው፥ በየ​ጭ​ፍ​ራ​ውም ይሰ​ፍ​ራሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለአ​ሮን ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየ​ጉ​ዞ​አ​ቸው ተጓዙ፤ ደመ​ና​ውም በፋ​ራን ምድረ በዳ ቆመ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጉዞ እን​ደ​ዚህ ነበር፤ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዙ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እያ​ን​ዳ​ንዱ በየ​ሥ​ር​ዐቱ፥ በየ​ዓ​ላ​ማው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ አን​ጻር ይስ​ፈሩ።


ሌዋ​ው​ያን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤ የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።


በለ​ዓ​ምም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ እስ​ራ​ኤል በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ሲጓዙ አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ መጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተ​ና​ገ​ረ​በት ቀን የአ​ሮ​ንና የሙሴ ትው​ልድ ይህ ነበረ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios