Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አንተ አለቃ ነህን? ደግ​ሞስ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር አገ​ባ​ኸ​ንን? እር​ሻ​ንና የወ​ይን ቦታ​ንስ አወ​ረ​ስ​ኸ​ንን? የእ​ነ​ዚ​ህ​ንስ ሰዎች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ታወ​ጣ​ለ​ህን? አን​መ​ጣም” አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህም በቀር አንተ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር አላመጣኸንም፤ ወይም ዕርሻዎችንና የወይን ተክል ቦታዎች አላወረስኸንም። ታዲያ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ታወጣለህን? በጭራሽ አንመጣም!”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላስገባኸንም፥ እርሻና የወይንም ተክል ቦታ አላወረስከንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ደግሞ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላገባኸንም፥ እርሻና ወይንም አላወረስኸንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዓይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም አሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 16:14
12 Referências Cruzadas  

“የሰ​ውን አዝ​መራ ከብ​ቱን ያስ​በላ፥ የሌላ ሰው ወይ​ን​ንም ያስ​በላ ሰው ቢኖር ግም​ቱን ይክ​ፈል። የሰ​ውን አዝ​መራ ፈጽሞ ቢያ​ስ​በላ ግን በአ​ጠ​ገቡ ባለ አዝ​መራ ልክ ይክ​ፈል፤ ወይ​ንም ቢሆን በአ​ጠ​ገቡ ባለ ወይን ልክ ይክ​ፈል።


“ስድ​ስት ዓመት ምድ​ር​ህን ዝራ፤ ፍሬ​ዋ​ንም አግባ፤


በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳ​ር​ፋ​ትም፤ የሕ​ዝ​ብ​ህም ድሆች ይበ​ሉ​ታል፤ እነ​ርሱ ያስ​ቀ​ሩ​ት​ንም የሜዳ እን​ስሳ ይብ​ላው። እን​ዲ​ሁም በወ​ይ​ን​ህና በወ​ይ​ራህ አድ​ርግ።


እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ከግ​ብፅ መከራ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ሀገር አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤


ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።


ነገር ግን እና​ንተ፦ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ አል​ኋ​ችሁ፤ እኔ ከአ​ሕ​ዛብ የለ​የ​ኋ​ችሁ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ወደ ላክ​ኸን ምድር ደረ​ስን፤ እር​ስ​ዋም ወተ​ትና ማር ታፈ​ስ​ሳ​ለች፤ ፍሬ​ዋም ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ከመ​ረ​ጠን ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ወደ​ዚች ምድር ያገ​ባ​ናል፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይሰ​ጠ​ናል።


ዘር ወደ​ማ​ይ​ዘ​ራ​በት፥ በለ​ስና ወይ​ንም፥ ሮማ​ንም፥ የሚ​ጠ​ጣም ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ክፉ ስፍራ ታመ​ጡን ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ች​ሁን?”


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ይዘው ዐይ​ኖ​ቹን አወ​ጡት፤ ወደ ጋዛም አው​ር​ደው በእ​ግር ብረት አሰ​ሩት፤ በግ​ዞ​ትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።


አሞ​ና​ዊው ናዖ​ስም፦“ ቀኝ ዐይ​ና​ች​ሁን ብታ​ወጡ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ ስድ​ብን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios