Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 15:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከዚያም ካህኑ፣ ባለማወቅ ኀጢአት ሠርቶ ለተሳሳተው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፤ ስርየት በሚደረግለትም ጊዜ ሰውየው ይቅር ይባላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ባለማወቅም ኃጢአት ሠርቶ ስሕተትን ለፈጸመው ለዚያ ሰው እንዲያስተሰርይለት፥ ካህኑ በጌታ ፊት ማስተስሪያ ያደርጋል፤ እርሱም ይቅር ይባላል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ካህኑ በስሕተት ኃጢአት ለሠራው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተስርይለት፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኃጢአት ሠርቶ ሳያውቅ፥ ለሳተ ለዚያ ሰው ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ይሰረይለትማል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 15:28
5 Referências Cruzadas  

በካ​ህ​ኑም እጅ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ዘይት ካህኑ በሚ​ነ​ጻው ሰው ራስ ላይ ያደ​ር​ግ​በ​ታል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ሳያ​ውቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥


እን​ዲ​ህም በወ​ይ​ፈኑ ያደ​ር​ጋል፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት በታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ አደ​ረገ እን​ዲሁ በዚህ ያደ​ር​ጋል፤ ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።


ስቡ ሁሉ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው የበግ ጠቦት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios