Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘኍል 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አሮ​ንም ሙሴን፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ስን​ፍና አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በድ​ለ​ን​ማ​ልና እባ​ክህ፥ ኀጢ​አት አታ​ድ​ር​ግ​ብን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሙሴንም እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፤ በስንፍናችን የሠራነውን ኀጢአት እባክህ አትቍጠርብን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አሮንም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ሆይ! ተሞኝተን ይህን አድርገናልና፥ ኃጢአትንም ሠርተናልና እባክህ፥ ኃጢአትን በእኛ ላይ አትቁጠርብን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አሮንም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ሆይ፥ በስንፍናችን ስለ ሠራነው ኃጢአት ይህ አሠቃቂ ቅጣት እንዲፈጸምብን አታድርግ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።

Ver Capítulo Cópia de




ዘኍል 12:11
15 Referências Cruzadas  

እር​ሱም ንጉ​ሡን አለው፥ “ጌታዬ! ኀጢ​አ​ቴን አት​ቍ​ጠ​ር​ብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በወ​ጣህ ቀን ባሪ​ያህ የበ​ደ​ል​ሁ​ህን አታ​ስ​ብ​ብኝ፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በል​ብህ አታ​ኑ​ር​ብኝ።


ሕዝ​ቡ​ንም ከቈ​ጠረ በኋላ ዳዊ​ትን ልቡ መታው፤ ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ባደ​ረ​ግ​ሁት ነገር እጅግ በድ​ያ​ለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስን​ፍና አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​አት ታርቅ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


ንጉ​ሡም ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “አሁን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለምን፤ እጄም ወደ እኔ ትመ​ለስ ዘንድ ስለ እኔ ጸልይ” አለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመነ፤ የን​ጉ​ሡም እጅ ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች። እንደ ቀድ​ሞም ሆነች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ላሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ኩኝ።”


እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።


ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እሳ​ቲ​ቱም ጠፋች።


ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ሞቶ እንደ ተወ​ለደ፥ ከተ​በላ ግማሽ ሥጋዋ ጋር ለሞት አት​ተ​ዋት።”


ሲሞ​ንም መልሶ፥ “ካላ​ች​ሁት ሁሉ ምንም እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ብኝ እና​ንተ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኑ​ልኝ” አለ።


እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ንጉሥ በመ​ለ​መ​ና​ችን በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨም​ረ​ና​ልና እን​ዳ​ን​ሞት ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን” አሉት።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios