Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንና አሕ​ዛ​ብን ዕድል ፈንታ አድ​ር​ገህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን ምድር፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን ምድር ወረሱ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “የአሕዛብን መንግሥታትና ነገሥታትን ድል ነሥተው፥ ከምድራቸው አዋሳኞች የሆኑትን ጠረፎች እንዲይዙ አደረግህ፤ ሲሖን የተባለ ንጉሥ ይገዛት የነበረችውን ሐሴቦን ተብላ የምትጠራውን ምድር፥ በድል አድራጊነት ያዙ፤ ዖግ የተባለው ንጉሥ ይገዛት የነበረችውንም የባሳንን ምድር ወረሱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 መንግሥታትንና አሕዛብን ከፍለህ ሰጠሃቸው፥ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 9:22
16 Referências Cruzadas  

እንደ ተጨ​ነ​ቁም ተመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰማ​ቸው፤


ምድ​ሪ​ቱን፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ​ትን ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን በታ​ላቅ ኀይ​ሌና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችው ክንዴ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ ለዐ​ይ​ኔም መል​ካም ለሆ​ነው እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ።


በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ በአ​ስ​ጣ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረ​ው​ንም የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ከገ​ደ​ሉት በኋላ፥


እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ፤ ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።


ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ቱት፥ በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅ​ራ​ቢያ ባለው ሸለቆ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፤


የእ​ር​ሱ​ንና የባ​ሳ​ንን ንጉሥ፥ የዐ​ግን ምድር፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን የሁ​ለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንን ነገ​ሥ​ታት ምድር ወሰዱ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios