Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አርባ ዓመ​ትም በም​ድረ በዳ መገ​ብ​ሃ​ቸው፤ ምንም አላ​ሳ​ጣ​ሃ​ቸ​ውም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ራ​ቸ​ውም አላ​በ​ጠም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በምድረ በዳ አርባ ዓመት መገብሃቸው፤ ምንም ያጡት አልነበረም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸውም አላበጠም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብካቸው፤ ምንም አላጡም፤ ልብሳቸው አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ረዳሃቸው፤ ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ምንም አላሳጣሃቸውም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸው አላበጠም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብሃቸው፥ ምንም አላጡም፥ ልብሳቸውም አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም።

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 9:21
9 Referências Cruzadas  

አጥ​ን​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይሉ​ሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ከሚ​ነ​ጥ​ቀው እጅ ታድ​ነ​ዋ​ለህ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ምድር እስ​ከ​ሚ​መጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አቅ​ር​ባ​ች​ሁ​ል​ኛ​ልን?


አርባ ዘመ​ንም በም​ድረ በዳ መገ​ባ​ቸው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ጅ​ህን ሥራ ሁሉ ባር​ኮ​ል​ሃ​ልና፤ ይህን ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ ምድረ በዳ እን​ዴት እንደ ዞር​ኸው ዕወቅ፤ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነበረ፤ ከተ​ና​ገ​ር​ኸው ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ሳ​ጣ​ህም።


አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ መራ​ችሁ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁም አላ​ረ​ጀ​ባ​ች​ሁም፤ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ላይ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።


የለ​በ​ስ​ኸው ልብስ አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ር​ህም አል​ነ​ቃም፤ እነሆ፥ አርባ ዓመት ሆነ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios