Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 መጥ​ተ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይወ​ጉና ያፈ​ር​ሷት ዘንድ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 መጥተውም ኢየሩሳሌምን ይወጉ ዘንድ፣ ሽብርንም ይፈጥሩ ዘንድ ሁሉም በአንድነት አደሙ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አየሁና ተነሣሁ፥ መኳንንቶቹን፥ ሹማምቱንና የተቀረው ሕዝብ፦ “አትፍሩአቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስታውሱ፥ ስለ ወንድሞቻችሁ፥ ስለ ወንዶች ልጆቻች፥ ስለ ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ስለ ሚስቶቻችሁና ስለ ቤቶቻችሁ ተዋጉ።” አልኳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህም በአንድነት ተባብረው ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣትና አደጋ ጥለው ሽብር ለመፍጠር በእኛ ላይ አድማ አደረጉ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 መጥተውም ኢየሩሳሌምን ይወጉና ያሸብሩ ዘንድ ሁሉም በአንድነት ተማማሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 4:8
11 Referências Cruzadas  

በርታ፤ ስለ ሕዝ​ባ​ች​ንና ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ከተ​ሞች እን​ጽና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዐ​ይኑ ፊት ደስ ያሰ​ኘ​ውን መል​ካ​ሙን ያድ​ርግ።”


“ጽኑ፥ አይ​ዞ​አ​ችሁ፤ ከእኛ ጋር ያለው ከእ​ርሱ ጋር ካለው ይበ​ል​ጣ​ልና ከአ​ሦር ንጉ​ሥና ከእ​ርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።


“አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ።


እኔም አል​ኋ​ችሁ፦ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አት​ፍሩ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios