Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አሞ​ና​ዊ​ውም ጦቢያ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “በድ​ን​ጋይ በሚ​ሠ​ሩት ቅጥ​ራ​ቸው ላይ ቀበሮ ቢወ​ጣ​በት ያፈ​ር​ሰ​ዋል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በአጠገቡም ቆሞ የነበረው አሞናዊው ጦቢያ፣ “ለመሆኑ የሚገነቡት ምንድን ነው? በድንጋይ የሚሠሩት ቅጥር እኮ ቀበሮ እንኳ ብትወጣበት ሊፈርስ ይችላል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ አምላካችን ጸለይን፥ በእነርሱም ምክንያት በሌሊትና በቀን በእነሱ ላይ ጠባቂ አቆምን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በአጠገቡም ቆሞ የነበረው ጦቢያ በበኩሉ፦ “እነርሱ ምን ዐይነት ቅጽር መሥራት ይችላሉ? የእነርሱ ግንብ ቀበሮ እንኳ ብትወጣበት ሊፈርስ ይችላል!” ሲል በማፌዝ ተናገረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አሞንዊውም ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ፦ በድንጋይ በሚሠሩት ቅጥራቸው ላይ ቀበሮ ቢመጣበት ያፈርሰዋል አለ።

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 4:3
8 Referências Cruzadas  

ሁለት የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም በፊቱ አስ​ቀ​ም​ጡና፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​ቦ​አል ብለው ይመ​ስ​ክ​ሩ​በት፤ አው​ጥ​ታ​ች​ሁም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በድ​ን​ጋይ መት​ታ​ችሁ ግደ​ሉት።”


“ተነ​ሥ​ተህ በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ አክ​ዓ​ብን ትገ​ናኝ ዘንድ ውረድ፤ እነሆ፥ ይወ​ር​ሰው ዘንድ በወ​ረ​ደ​በት በና​ቡቴ የወ​ይን ቦታ ውስጥ አለ።


አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተወ​ራ​ረድ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላ​ጥና አገ​ል​ጋዩ አሞ​ና​ዊው ጦብያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መል​ካ​ምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበ​ሳጩ።


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥ​ሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍ​ራ​ሹም አን​ዳች እን​ዳ​ል​ቀ​ረ​በት ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦቢያ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም የቀ​ሩ​ትም ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ድረስ በበ​ሮቹ ውስጥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አላ​ቆ​ም​ሁም ነበር።


የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።


“አሞ​ናዊ ወይም ሞዓ​ባዊ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios