Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሥ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ ሀገር እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ሱኝ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ገዦች ደብ​ዳቤ ይስ​ጠኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ደግሞም እንዲህ አልሁት፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በደኅና እንዲያሳልፉኝ ከኤፍራጥስ ማዶ ላሉት አገረ ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡ መልካም ፈቃዱ ቢሆን፥ ይሁዳ እስክደርስ ድረስ እንዲያሳልፉኝ ከወንዙ ማዶ ላሉት ገዢዎች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ንጉሡንም፦ “ንጉሡ ደስ ቢለው፥ እስከ ይሁዳ አገር እንዲያደርሱኝ በወንዝ ማዶ ላሉት አገረ-ገዦች ደብዳቤ ይሰጠኝ፤

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 2:7
6 Referências Cruzadas  

“አሁ​ንም አንተ በወ​ንዝ ማዶ ያለ​ኸው የሀ​ገሩ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አሰ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ በወ​ንዝ ማዶም ያሉ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ችሁ አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያን ከዚያ ራቁ፤


እኔም ንጉሡ አር​ተ​ሰ​ስታ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ግምጃ ቤቶች ሁሉ ይህን ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቻ​ለሁ፦ የሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ካህኑ ዕዝራ ከእ​ና​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገ​ውን ሁሉ አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤


ንጉ​ሡ​ንም፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ በሚ​ሹት ሁሉ ላይ ለመ​ል​ካም ነው፤ ኀይ​ሉና ቍጣው ግን እር​ሱን በሚ​ተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተና​ግ​ረን ነበ​ርና፤ በመ​ን​ገድ ካለው ጠላት ያድ​ኑን ዘንድ ጭፍ​ራና ፈረ​ሰ​ኞች ከን​ጉሡ እለ​ምን ዘንድ አፍሬ ነበ​ርና።


የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ በወ​ንዙ ማዶ ላሉት ለን​ጉሡ ሹሞ​ችና ገዢ​ዎች ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አከ​በሩ።


በወ​ን​ዙም ማዶ ወዳ​ሉት ሀገረ ገዦች መጥቼ የን​ጉ​ሡን ደብ​ዳ​ቤ​ዎች ሰጠ​ኋ​ቸው። ንጉ​ሡም ከእኔ ጋር የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለ​ቆ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ልኮ ነበር።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ገባ​ዖ​ና​ዊው መል​ጥ​ያና ሜሮ​ና​ታ​ዊው ያዴን፥ እስከ ወን​ዙም ማዶ አለቃ ግዛት የሆኑ የገ​ባ​ዖ​ንና የመ​ሴፋ ሰዎች ሠሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios