Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ነህምያ 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት፥ ስለ ኅብ​ስተ ገጽም፥ ዘወ​ት​ርም በሰ​ን​በ​ትና በመ​ባቻ ስለ ማቅ​ረብ ስለ እህሉ ቍር​ባ​ንና ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ ስለ በዓ​ላ​ትም፥ ስለ ተቀ​ደ​ሱ​ትም ነገ​ሮች፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስለ​ሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ይህም በጠረጴዛው ላይ ለሚቀርበው ገጸ ኅብስት፣ ዘወትር ለሚቀርበው የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በሰንበት፣ በወር መባቻና በተደነገጉ በዓላት ለሚቀርበው መሥዋዕት፣ ለተቀደሱ መባዎች፣ ለእስራኤል ስርየት ለሚቀርበው የኀጢአት መሥዋዕትና ለአምላካችን ቤት ሥራ ሁሉ የሚውል ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ለአምላካችን ቤት አገልግሎት የሚውል አንድ ሦስተኛ ሰቅል በየዓመቱ ለመስጠት በራሳችን ላይ ትእዛዝ እናስቀምጣለን። ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቁርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እንዲሁም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ከዚህ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልተን እናቀርባለን፦ ይኸውም የተቀደሰውን ኅብስት፥ በየዕለቱ መቅረብ የሚገባውን የእህል መባ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑትን እንስሶች፥ በሰንበት ቀኖች፥ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ጊዜና በሌሎችም በዓላት የሚቀርበውን፥ ሌላውንም የተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ ኃጢአት ማስተስረያ መቅረብ የሚገባውንና ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ሌላውንም ነገር ሁሉ አናስታጒልም።

Ver Capítulo Cópia de




ነህምያ 10:33
7 Referências Cruzadas  

እነሆ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ታዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የጣ​ፋ​ጩን ሽቱ ዕጣን ለማ​ጠን፥ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት ለማ​ኖር፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በጥ​ዋ​ትና በማታ፥ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ለማ​ቅ​ረብ እኔ ልጁ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠ​ራ​ለሁ፤ እር​ሱ​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


የማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ው​ንም ገን​ዘብ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወስ​ደህ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ እን​ዲ​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ይሁን።”


እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ።


ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios