Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 27:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ካሾፉበት በኋላም ቀዩን ልብስ ገፍፈው የራሱን ልብስ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ይዘውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከአፌዙበትም በኋላ ካባውን ገፈው የራሱን ልብስ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ካፌዙበት በኋላ ቀዩን ልብስ አውልቀው የራሱን ልብስ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ይዘውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 27:31
12 Referências Cruzadas  

ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”


እነ​ሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ አክ​ዓብ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያ​ለ​ህን? እነሆ፥ ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።


እርሱ ግን በመ​ከ​ራው ጊዜ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም፤ እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሸ​ላ​ቾቹ ፊት ዝም እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ሰው​ዬው ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት” አለው።


ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።


ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት።


ለደቀ መዛሙርቱ “ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል፤” አለ።


ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።


ከዚህ በኋላ ሊሰ​ቅ​ሉት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ተቀ​ብ​ለው ወሰ​ዱት።


ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዝ​ሙ​ሩን፥ “እና​ትህ እነ​ኋት” አለው፤ ከዚ​ያ​ችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝ​ሙሩ ተቀ​ብሎ ወደ ቤቱ ወሰ​ዳት።


ከከ​ተ​ማም ወደ ውጭ ጐት​ተው አው​ጥ​ተው ወገ​ሩት፤ የሚ​ወ​ግ​ሩት ሰዎ​ችም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ሳውል በሚ​ባል ጐል​ማሳ እግር አጠ​ገብ አስ​ቀ​መጡ።


ስለ​ዚ​ህም ኢየ​ሱስ ሕዝ​ቡን በደሙ ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ ከከ​ተማ ውጭ ተሰ​ቀለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios